Connect with us

ሳይንት-ምንትዋብ፤ 

ሳይንት-ምንትዋብ፤ አስደናቂው ብሔራዊ ፓርክ
ሄኖክ ስዩም

ባህልና ታሪክ

ሳይንት-ምንትዋብ፤ 

ሳይንት-ምንትዋብ፤ 

አስደናቂው ብሔራዊ ፓርክ

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ቦረና ሳይንት ብሔራዊ ፓርክ ሊወስደን ነው፡፡ ከፍተኛ ሥነ-ምህዳር ያለው ይህ ድንቅ የሀገራችን ብሔራዊ ፓርክ ውብ ደኖች፣ አስደናቂ ዋሻዎችና ማራኪ መልከዓ ምድሮች አሉት ይለናል በተከታዩ ዘገባው፡፡)

(ሄኖክ ስዩም ~ በድሬ ቲዩብ)

ከመካነ ሰላም ተነሳሁ፡፡ ሳይንት መሃል አማራ ነው፡፡ የታሪክ እንብርት፡፡ ውብ ታሪክ ባለው ሀገር ወደሚገኝ ውብ ተፈጥሮ ነው የመጣሁት፤ በአዋጅ የታወጀው ስሙ የቦረና ሳይንት ወረሂመኑ ብሔራዊ ፓርክ ተብሎ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ረዥሙ የብሔራዊ ፓርክ ስም፤

በ2001 ቀድሞ ደንቆሮ ጫካ እና ምንትዋብ ደን ይባል የነበረው ስፍራ ወደ ብሔራዊ ፓርክነት ቦረና ሳይንት የሚለውን ስም ይዞ ተቋቋመ፡፡ ቀበሌያቱ ሲሰፉ ወረሂመኑ ተጨመረ፡፡ ወደ ፓርኩ ቅጥር እየገባሁ ነው፡፡

ደጋና ወይና ደጋ ነው፡፡ ከፍታው በጨመረ ቁጥር ቅዝቃዜው ያይላል፡፡ ገና ከመግቢያው የሚታየው ውበት ለመድረስና ጨርሶ ለማየት ያጓጓል፡፡ የአስታና የጅብራ ውበት ተቀበለኝ፡፡ ቀድሞ መድረስ የፈለግሁት ወደ ትልቁ ዋሻ ነው፡፡ 

ከሰላሳ በላይ ጡት አጥቢዎ ዱር እንስሳት ዝርያዎች ይኖሩበታል፡፡ የቀይ ቀበሮ መኖሪያ፤ የምኒልክ ድኩላ ምድር፣ የጭላዳዎች መፈንጫ፡፡ 

ሶስት ሜትር የሚወፈር ዝግባ የሚንዠረገግበት፣ እድሜ ጠገቡ ዛፍ ዘመኑን የኖረበት፡፡ ከሚነገር ሲታይ ልብ የሚያደርስ፣ መልከዓ ምድራዊ ውበቱ ልዩ ነው፡፡ ትንሽ ቦታ ግን የማይለካ ውበትና ድምቀት፡፡

ከ354 በላይ የእጽዋት ዝርያ፤ ምነው ወፍ በሆንኩና በበርሁ የሚያስብል፤ እየዛፉ ቅርንጫ ጫፍ ለመንጠልጠል የሚያስመኝ፤ ደግሞ የሚዘናፈለውን ጓሳ ዳብሰው ዳብሰው አስብሎ ምድር የሚያስዳስስ፣ መንገድ የማይመስል ውብ ጎዳና፤ የገነት ውስጥ ማለፊያ ወደ ዋሻው የሚወስድ… ዋሻው ድረስ አብረን እንሄዳለን፡፡ 

ቁልቁል ደንቆሮ ጫካን አየሁት፡፡ እዚያ ገብቶ መደማመጥ የለም ይላል ሀገሬው፡፡ እዚህ ቆም ግን ደንቆሮን መስማት ይቻላል፡፡ ሲናገር፣ ውበቱን በውዝዋዜ ድምጹ ሲያሰማ፤ ቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሔራዊ ፓርክ፡፡ ወደ ዋሻው እየቀረብን ነው፡፡

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top