Connect with us

ኢትዮጵያም ሞት-የመንም ሞት፤ ኢትዮጵያውያን የማንሞተው የት ነው? 

ኢትዮጵያም ሞት-የመንም ሞት፤ ኢትዮጵያውያን የማንሞተው የት ነው?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ኢትዮጵያም ሞት-የመንም ሞት፤ ኢትዮጵያውያን የማንሞተው የት ነው? 

ኢትዮጵያም ሞት-የመንም ሞት፤ ኢትዮጵያውያን የማንሞተው የት ነው? 

(ስናፍቅሽ አዲስ – ድሬቲዩብ)

የትም የምንሞት ህዝቦች መሆናችን ሞታችንን የከፋ ያደርገዋል፡፡ ዓለም ቢገድለንና ቢያሳድደን አይገርምም የሚገርመው በዚህ ሞት የትም በሚያሳድደን ዓለም ላይ እርስ በእርስ የምንገዳደልም መሆናችን ነው፡፡ በወለጋ ስለሞቱ ኢትዮጵያውያን ዜና አደመጥን፤ መርዶው ግን ዜናው መልኩን ቀይሮም አልተቀየረም፡፡ የውጪ ዜና ስናደምጥ አሁንም ኢትዮጵያዊያን በየመን መሞታችንን ነገረን፡፡

ገዳዮቻችን ላይ ልዩነትና ውዝግብ ቢኖርም ሟቾች ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ በትግራይ ለሚሞተው ወገን ህወሃትም ተጠየቀች መንግስት ኢትዮጵያዊ ግን ሞቷል ተሰዷል፡፡ ገዳይና ሟች ላይ ሙግት ብንገጥምም በመተከል ያለቀው ግን ብዙ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወለጋ ሌላ የሞት ዜና መምጫ ዳግም የመርዶ ቀጠና ሆነ፡፡

ኢትዮጵያውያን የማንሞተው የት ነው ብለን ብንጠይቅ መልስ የለውም፡፡ የትም እንሞታለን፡፡ በቀዬውና በተወለደበት መጤ ተብሎ የሚገደል የዓለም ዜጋ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው፡፡ ፖለቲከኞች በሰከሩ ቁጥር እንደ ጠርሙስ የሚከሰከሰው ነፍስ የኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲ ልጁን ልኮ እሬሳ የሚታቀፈው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በሰላም ሀገር ሞት ስጋት የሚሆንበት ህዝብም ቢሆን ከኢትዮጵያ ውጪ ያለ አይመስለኝም፡፡

የሞታችን ምክንያቱ ለሰሚው ግራ ነው፡፡ አንድ ሰው በመሞቱ ለማዘን አንድ ሺህ ሰው ገድለን ዳግም ሀዘን እንቀመጣለን፡፡ ደስታችንም ሆነ ሀዘናችን ከመግደልና ከመሞት ጋር ተቆራኝቷል፡፡ መሳሪያ ያነገቡ ነጻ አውጪዎች ንጹህ ካልገደሉን ጀብዳቸው ከንቱ ይሆንባቸዋል፡፡ ንጹሃን ሞታቸው ፍልሚያ የገባ ሠራዊት ያህል የማይገርምና የሚጠበቅ ሆኖብናል፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስለምርጫ ስለ ሰላም እናወራለን፡፡ ለእርቅ የተሰበሰቡ ሰዎች ታጠቀው ከተፍ ባሉ ሽፍቶች ይረሸናሉ፡፡ በአማሮ ወረዳ የሆነውን ስንሰማ የት ነው የማንሞተው? ብለን እንጠይቃለን፡፡ የመንግስት አመራሮች ጭምር የሞትን ጽዋ የሚጎነጬበት ታሪክ ላይ ደርሰናል፡፡ ያልታወቁ ታጣቂዎች የገዳዮቻችን የዳቦ ስም ነው፡፡ የምንሞተው ግን የታወቅነው ኢትዮጵያውያን ነን፡፡

በንጹሃን ሞት ፖለቲካ የመነገድ ባህል አድጎ አድጎ የሟች ኢትዮጵያውያን ቁጥር ጨምሯል፡፡ ለኢትዮጵያዊ የሞቱ ምክንያት ማንነቱ ነው፡፡ በብሔሩና በሃይማኖቱ ምክንያት በምድር ላይ እንዳይኖር ይፈረድበታል፡፡ በሴቶችና በእናቶች ላይ የሚደርሰው መከራ ስቃይና ስደት ከሞት መትረፍ ምን ጥቅም አለው የሚያስብል ነው፡፡

መተከል የደም መሬት ሲሆን ነፍሳቸውን ለማትረፍ ሙሉ ቤታቸውን ትተው የተሰደዱት ወገኖቻችን ዛሬም ስደተኞችና ቤት አልባዎች ሆነው በችግር ይሰቃያሉ፡፡ ከትግራይ የተሰደዱት ወገኖቻችን ወደ ቀዬያቸው አልተመለሱም፡፡ ወገን እንዳይሰደድ ከማሰብ ይልቅ ግን ዛሬም ለስደት የሚያበቃ ሞት በዜጎቻችን ላይ ይቆጠራል፡፡ ኢትዮጵያዊ ይሞታል፡፡ ከስንት አንድ ጊዜ ዜና ይሆናል፡፡ ዜና ሳይሆን የሚሞተው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ የትም ግን የሚሞተው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top