Connect with us

የመንግስታችን ነገር፡-  የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ያደረኩልኸ እኔ ነኝ!

የመንግስታችን ነገር፡- የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ያደረኩልኸ እኔ ነኝ!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የመንግስታችን ነገር፡-  የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ያደረኩልኸ እኔ ነኝ!

የመንግስታችን ነገር፡-  የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ያደረኩልኸ እኔ ነኝ!

(ጫሊ በላይነህ)

“መንግሥት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ የዋጋ ግሽበቱ እንዳይባባስ እየሰራ ነው“ ስለመባሉ ሰማን፡፡ ይኸን ያሉት የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ናቸው፡፡ የዘገበው ደግሞ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ነው፡፡ 

የመንግስታችን ሀሳብ ጥሩ ነው፤ ግን መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር ስለመጣጣሙ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡

ሚኒስትሩ እንዲህ ይላሉ፡፡ “የዋጋ ግሽበቱ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ መታየት የጀመረ ነው። መንግሥት ከ2010 ዓ.ም ወዲህ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ የዋጋ ግሽበቱ እንዳይባባስ እያደረገ ነው።

በተለይም ከውጭ በሚገባው የምግብ ዘይት ላይ እስከ 58 በመቶ የሚደርስ የታክስ ቅናሽ በማድረግ ገበያውን ለማረጋጋት መንግሥት መሥራቱን፤ የነዳጅ ጭማሪ ሲከሰትም በማረጋጊያ ፈንድ አማካኝነት ዋጋው እየተስተካከለ የኑሮ ጫና እንዳይፈጠር ተደርጓል፡፡

በአንዳንድ አገራት የዋጋ ግሽበት ከ126 እስከ 333 በመቶ ጨምሯል ያሉት ሚኒስትሩ፣ የዋጋ ግሽበቱን ለመከላከል ከ2010 ዓ.ም ወዲህ የተሰሩ በርካታ የማሻሻያ ሥራዎች አሁን ላለንበት ሁኔታ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል። 

ሥራዎች ቀድመው ባይሰሩ ኖሮ አሁን እየታየ ያለው ግሽበት እንደሌሎች አገራት በጣም ሊከፋ እንደሚችል ገልጸዋል።”

እንግዲህ ክቡር ሚኒስትሩ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ይህቺ ምን አላት፣ ቻሉት እያሉን ነው፡፡ ያው ነገሩ እኛ አስቀድመን ባናስብላችሁ ኖሮ ጅብ ይበላችሁ ነበር ነው፡፡

በሌላ በኩል የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ የየካቲት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 20 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን ሰሞኑን ይፋ አድርል፡፡ የጥር ወር አጠቃላይ ግሽበት 19 ነጥብ 2 ነበር  ፤ በየካቲት ወር የ4 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ 20 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል፡፡

የየካቲት ወር ምግብ ዋጋ ግሽበት  ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ22 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል። በእህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም የቀጠለ ሲሆን ለምግብ ዋጋ ግሽበት መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ኤጀንሲው ገልጿል።

በሌላ በኩል ስኳር፣ የምግብ ዘይት፣ ቅመማ ቅመም በርበሬ፣ ድንች እና ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ  የዋጋ ግሽበት የየካቲት ወር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ፈጣን ዕድገት አሳይቷል ተብሏል።

የዋጋ ግሽበት ከሁለት ዲጂት በላይ ከወጣ እጅግ አደገኛ ነው ሲል እምብዛም ኢኮኖሚ ዕውቀት ለሌለን ዜጎች አስቀድሞ የነገረን ይኸው መንግስታችን ነበር፡፡ ንረቱ የሰውን ኪስ እያራቆተ ነው፡፡ በወር ገቢ የሚተዳደረውን ሕዝብ እያስራበ ነው፡፡ 

የዋጋ ንረቱ በሕዝቡ ዕለት ምግብ በዳቦና በእንጀራ ላይ ጭምር እየተንጸባረቀ ነው፡፡ በቤት ኪራይ፣ በትራንስፖርት ሕዝብ ዋጋ እየከፈለ ነው፡፡ ለዚህ ኑሮ አብዝቶ ለደቆሰው ሕዝብ፤ የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ያደረኩልኸ እኔ ነኝ ማለት ትርጉሙ ምን ይሆን?

ለመሆኑ በገጠመኝ ከየመጋዘኑ በተሰበሰበ ዘይት እና ሸቀጥ የሀገር የዋጋ ንረት ማረጋጋት እንደምን ተቻለ? ደግሞስ ማረጋጋቱ ምንነው አልታየ አለ? ለግሽበት የዳረገን ትክክለኛ ሕመሙን ደብቆ መድሃኒት መፈለግስ ይቻላልን?

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top