Connect with us

‹‹በትግራይ ክልል ለሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ 65 ሺህ ዜጎች እርዳታ ተከፋፍሏል፡፡›› አቶ ምትኩ ካሳ የፌዴራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር

‹‹በትግራይ ክልል ለሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ 65 ሺህ ዜጎች እርዳታ ተከፋፍሏል፡፡›› አቶ ምትኩ ካሳ የፌዴራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር
አብመድ

ዜና

‹‹በትግራይ ክልል ለሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ 65 ሺህ ዜጎች እርዳታ ተከፋፍሏል፡፡›› አቶ ምትኩ ካሳ የፌዴራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር

‹‹በትግራይ ክልል ለሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ 65 ሺህ ዜጎች እርዳታ ተከፋፍሏል፡፡›› አቶ ምትኩ ካሳ የፌዴራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር

በትግራይ ክልል ለችግር ለተጋለጡ 3 ሚሊዮን አንድ መቶ 65 ሺህ ዜጎች የተለያዩ እርዳታዎች መከፋፈላቸውን የፌዴራል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ አስታውቀዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ  ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፣ በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በተፈጠረ ሰብዓዊ ቀውስ በርካታ ወገኖች ለችግር የተጋለጡ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ኮሚሽኑ ባደረገው ጥረት ለ3 ሚሊዮን አንድ መቶ 65 ሺ ወገኖች የተለያዩ ድጋፎች ተደርገዋል።

በአካባቢው የነበረው ችግር ከባድ የነበረ ቢሆንም ሰብዓዊ ድጋፉ ላይ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግና ኮሚሽኑም ጠንካራ ሥራ በመሥራቱ እርዳታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ለ 3 ሚሊዮን አንድ መቶ 65 ሺ ዜጎች ምግብ ነክ አቅርቦቶችን ማቅረብ መቻሉን አስታውቀዋል።

በእርዳታ አሰጣጡ በኩል በተለይም መንግሥት ያደረገው ጥረትና ተሳትፎ ላቅ ያለ ነው ያሉት አቶ ምትኩ 10 የሚጠጉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም በአካባቢው ላይ የሚታየውን ሰብዓዊ ችግር ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በመቀሌ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተወካዮች፣ የክልል ሴክተር ቢሮዎች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮችና ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችን ያቀፈ በመሆኑ ለችግሩ ሰፋ ያለ ምላሽ እንዲሰጥ አስችሏል ፤ በዚህ ምክንያትም እርዳታ ያገኙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በአካባቢው የትራንስፖርት፣ የጸጥታ ሁኔታ እንዲሁም መንግሥታዊ መዋቅሩ መፍረሱ በእርዳታ አሰጣጡ ላይ ከፍ ያለ ችግር ሲፈጥር እንደነበር የገለጹት አቶ ምትኩ፤ አሁን ላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የዞን አስተዳደሮች እንዲቋቋሙ በማድረጉና እነሱም ደግሞ የወረዳ አስተዳደሮችን በማቋቋማቸው እርዳታው ወደ እያንዳንዱ ግለሰብ እየደረሰ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከጸጥታ ጋር በተያያዘም አንዳንድ አስቸጋሪ ቦታዎች እንዳሉ ገልጸው፣ ወደነዚህ አካባቢዎች እርዳታዎች በሚጓጓዙበት ወቅት መከላከያ ሰራዊቱ እጀባ ስለሚያደርግ እስከ አሁን የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች ለደህንነታቸው በመስጋት እርዳታውን ለማዳረስ ፍቃደኛ እንዳልነበሩ ጠቁመው፣ አሁን ሁኔታዎች እየተሻሻሉ በመምጣታቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም 30 መኪኖችን ድጋፍ አድርጓል ፤ የትራንስፖርት መኪኖችም አገልግሎትን እየሰጡ ነው ፤ በኮሚሽኑ ስር ያለው የዕለት ደራሽ ትራንስፖርት ድርጅትም ወደ አካባቢው ገብቶ አገልግሎቱን እየሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሌሎች አራት የግል ትራንስፖርት ድርጅቶችም የእርዳታ አሰጣጡ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን አመልክተዋል።(አብመድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top