Connect with us

አዲስ አበባ ከተማ በክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ በክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ ፡፡
Photo: Social media

ዜና

አዲስ አበባ ከተማ በክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ በክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ ፡፡

ሸራተን አዲስ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ በክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ስም እንዲሰየምና  ሃውልት ለመስራትም የመሰረተ ድንጋይ መቀመጡን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

በወዳጅነት አደባባይ  “ቆሜ ልመርቅሽ ” ዝክረ አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ  የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አንዳንድ ለየት ያሉ ሰዎች አሉ ሀገር ገንተው ሀገር ሆነው የሚጠሩ፤በሙያቸው በርካቶችን ማርከው የተግባራቸው ተጋሪ የሚያደርጉ ሀገር እና ማህበረሰቡን የሚገልጹ ሰዎች ይፈጠራሉ ብለዋል፡፡

ጥላሁን የኢትዮጵያ መስታወት ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች በደስታዋ የፈነደቀ በሀዘኗ ያለቀሰ ለጀግንነቷ ግንባር ድረስ የዘመተ ውድ ልጅ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ጥላሁን ጥላ ሆኖ በርካቶችን ያስጠለለ፣ሀገር ወዳድ ባለሙያዎች እንዲፈጠሩ አርዓያ መሆን የቻለ በትውልዶች መካከል ክስተት ሆኖ የተገኘ ባለሙያ ለዚህም ነው ጥላሁን ሀገር ነው የምንለው ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ኘሮግራሙን ያስተባበሩትን አካላትና የገንዘብ ድጋፍ ያደረገውን ህዝብ አመስግነዋል። “የዝክረ ጥላሁን ገሠሠን ዝግጅት በማስተባበር፣ የተገኘው ገቢ ለ’ገበታ ለሀገር’ እንዲውል ያደረጋችሁ ሁሉ ምስጋናዬ እና አድናቆቴ ይድረሳችሁ። ለተሰበሰበው ከ80 ሚሊየን የሚበልጥ ገንዘብ መዋጮ ያደረጋችሁ ሁሉ የማይደበዝዝ አሻራችሁን በኢትዮጵያ ልማት ላይ አሳርፋችኋል” ብለዋል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top