Connect with us

“17 ሚሊየን ሊትር ዘይት በሀገር ውስጥተመርቶ ወደ ገበያ ገብቷል” ንግድና ኢንደስትሪ ሚ/ር

"17 ሚሊየን ሊትር ዘይት በሀገር ውስጥተመርቶ ወደ ገበያ ገብቷል" ንግድና ኢንደስትሪ ሚ/ር
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

“17 ሚሊየን ሊትር ዘይት በሀገር ውስጥተመርቶ ወደ ገበያ ገብቷል” ንግድና ኢንደስትሪ ሚ/ር

“17 ሚሊየን ሊትር ዘይት በሀገር ውስጥተመርቶ ወደ ገበያ ገብቷል” ንግድና ኢንደስትሪ ሚ/ር

መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማስተካከል በርካታ ስራዎችን እየሠራ መሆኑን የጠቀሱት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር  አቶ መላኩ አለበል መንግስት በርካታ የውጭ ምንዛሬ በማፍሰስ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የህብረተሰቡን የኑሮ ሂደት ያሻሽላሉ ያላቸውን ምርቶች በማከማቸትና በመሰወር የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት በሚጥሩ የንግድ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በመቆጣጠር የህብረተሰቡን የኑሮ ደህንነት ለማስጠበቅ ከሚሰራው የክትትልና ቁጥጥር ስራ ጎን ለጎን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡ 

የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦትና ፍላጎትን በማሟላት የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በተሰራው ስራ ትልልቅ የዘይት ፋብሪካዎች ተገንብተው በያዝነው የካቲት ወር ወደ ምርት በመግባት 17 ሚሊዬን ሊትር ዘይት ወደ ገበያ ያስገቡ መሆኑን የገለፁት አቶ መላኩ 58% ቀረጥና ተያያዥ ክፍያዎች ይጣልባቸው የነበሩ እንደ ዘይት፣ የህፃናት አልሚ ምግቦችና ሌሎች መሰረታዊ ምግብ ነክ ገቢ ምርቶች ወደ 5% ዝቅ በማድረግ የገበያ የንግድ ስርዓቱን ለማሻሻል እየተሰራ ነው፡፡ 

የኑሮ ውድነትን በቁጥጥር ክትትልና እርምጃ በመውሰድ ብቻ ማሻሻል አይቻልም ያሉት አቶ መላኩ ምርትና ምርታማነትን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማሻሻል ፍላጎትና አቅርቦቱን ለማጣጣም መንግስት ለግብርናውና አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በተወሰደው የለውጥ ስራ መንግስት የሰራተኞችን ደመወዝ የመክፈል አቅም አልነበረውም ያሉት ሚኒስትሩ የሀገራችን የውጭ የዕዳ ጫናና ብድር የመክፈል አቅም በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ በአበዳሪ ሀገራት ዘንድ የነበራት ተዓማኒነት የወረደ የነበረ መሆኑን ጠቅሰው የለውጥ አመራሩ በወሰደው አርምጃ በርካታ እዳዎች በመከፈላቸውና የሀገራትን በሌሎች ሀገራት ዘንድ ያላት እምነት እንዲሻሻል በማድረግ  ብድር ለማግነትና የዕዳ የመክፈያ ጊዜውን ለማራዘም በተሰራው ስራ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡

የአለም የኢኮኖሚ ዕድገት በኮሮና ወረርሽ በተፈተነበት በዚህ ወቅት ሀገራችን ያስመዘገበችው የኢኮኖሚ ዕድገት ከአለም ሀገራት ቀዳሚ ያደርጋታል፡፡

333 በመቶ የዋጋ ንረት የታየባቸው ሀገራት ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት  ሀገራችን በጎርፍ አደጋ፣ በአንበጣ መንጋና ህግን የማስከበር ስርዓቱ ብትፈተንም  የሀገራችን የሸቀጦች አማካኝ የዋጋ ንረት 19.2 በመቶ መሆኑን የገለፁት  አቶ መላኩ መንግስት የንግድ ስርዓቱን በማዘመን፣ የአቅርቦትና ፍላጎት ልዩነቱን ለማጥበብና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ አማካኝ የዋጋ ንረቱን ወደ 13 በመቶ ዝቅ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡(ንኢሚ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top