Connect with us

ጦርነትን የሚጣላው፤ ጦርነትን የሚያሸንፈው፤ ንጉሣችን ምኒልክ የአድዋ ፈጣሪ፡፡    

ጦርነትን የሚጣላው፤ ጦርነትን የሚያሸንፈው፤ ንጉሣችን ምኒልክ የአድዋ ፈጣሪ፡፡
ሄኖክ ስዩም

ባህልና ታሪክ

ጦርነትን የሚጣላው፤ ጦርነትን የሚያሸንፈው፤ ንጉሣችን ምኒልክ የአድዋ ፈጣሪ፡፡    

ጦርነትን የሚጣላው፤ ጦርነትን የሚያሸንፈው፤ ንጉሣችን ምኒልክ የአድዋ ፈጣሪ፡፡    

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)

እንደ ምኒልክ ጦርነትን ማን ይጠላታል? በሁሉም ውጊያዎች አስቀድሞ ደም አይፍሰስ ብሎ የሚማጸን ንጉሥ ነው፡፡ በሚለምነው ጦርነት ብልጫውን ያውቀዋል፡፡ በሚሸሸው ጦርነት ድሉ እጁ እንደሆነ ያምናል፡፡ ግን ለድል ሲል ደም እንዲፈስ የማይናፍቅ ጀግና ነው፡፡

እነሆ የአድዋ ዋዜማ፤ እኛ አድዋን ከምኒልክ አንነጥለውም፡፡ ዓለም ባለቤቱን በሚያውቀው ጦርነት እኛ አዲስ ነገር አንፈጥርም፡፡ የአድዋ ፈጣሪዋ ምኒልክ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ደግሞም እምዬ እንለዋለን፡፡ እንደ እናት የሚራራ፣ እናት ሀገሩን የሚወድ የጥቁር ቀለም ሁሉ የኩራት እናት የሆነ እምዬ ምኒልክ፡፡ ጥቁሩ ንጉሥ፤

አድዋ ዘንድሮ በድፍን ኢትዮጵያ ተክብሯል፡፡ ለተከታታይ አመታት አድዋን ባለማክበር የታላቁን ንጉሥ ክብር ለመሸፈን የተደረገው ጥረት መልኩን የቀየረ መስሎኛል፡፡ አድዋን እያከበሩ ፈጣሪውን መጋረድ ወደሚል አዲስ ስልት፤ ምኒልክ ዓለም ነው፡፡ 

ማንም የትም እንዴትም የማይጋርደው፡፡

አድዋ የጋራ ምልክታችን ነው፡፡ አባቶቻችን በአንድ ስም፤ በአንድ ቀለም፤ በአንድ መንፈስ፤ አንድ ንጉሥ መርቷቸው ድል ያደረጉበት ልዩ ቀን፡፡ ስለዚህ ቀን ክብር አብሮ መቆም ዳግም የአድዋ አይነት ነጣጥሎ ጣይ መንፈስ በእኛነታችን ላይ ድርሻ እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡

ዛሬ ዋዜማ ነው፡፡ ከዋዜማው በፊት ደብረ ብርሃን፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ታቦር አድዋን በድምቀት ዘክረውታል፡፡ 

በመንግስት ደረጃ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ሀረርና ሀዋሳም ተከብሯል፡፡ አድዋ ዓለም ከሚያውቅልን ድንቅ ገድል አንዱና ዋናው ነው፡፡ ዓለም ዘንድም የምንታወቅበት፡፡ 

አድዋን የምንዘክረው፣ አድዋን የምናስበው ከንጉሠ ነገሥታችን ነጥለን አይደለም፡፡ በጎሏ ተደስተን ካገባት የምንጣላ የእግር ኳስ ደጋፊዎች አይደለንም፡፡ ጎሏንም፣ ማሸነፋችንንም ያገባትን ጎበዝ ተጫዋቻችንንም እኩል የምንወድ የድል አድራጊዎች ልጆች ነን፡፡

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top