Connect with us

አረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት (አረና) ጠንከር ያለ መግለጫ አወጣ፡፡

አረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት (አረና) ጠንከር ያለ መግለጫ አወጣ፡፡
Photo: Social media

ዜና

አረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት (አረና) ጠንከር ያለ መግለጫ አወጣ፡፡

አረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት (አረና) ጠንከር ያለ መግለጫ አወጣ፡፡

ስድስት ነጥቦቹን አጠር አድርገን በማቅረብ ዝርዝር የመግለጫውን ቅጂ አያይዘናል፡፡

  1. በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት የዕለት ደራሽ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ቁጥራቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የዕለት ደራሽ ዕርዳታ የሚከፋፈልበት መላ እንዲፈለግ፣
  2. የመንግስት ተቋማት ባሉባቸው አካባቢዎች ሕዝቡ የዕለት ተዕለት ተግባሩን የሚያከናውንበት ሁኔታ ይፈጠር ዘንድ ተቋማት እንዲከፈቱና የወደሙ መሰረተ ልማቶች እንዲገነቡ ከወዲሁ የተቀናጀ የመልሶ ማልማት ዕቅድና ዝግጅት ተደርጎ እንዲጀመር፣
  3. ሕገመንግስታዊ ዕውቅና ያለው የትግራይ ክልል ከጦርነቱ በሃላ ከፊሉ በአማራ ክልል ቁጥጥር  ስር መዋሉን በማጤን ይህ አካሄድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋጥ ሊፈጥር ስለማይችል ማንኛውም የይገባኛልና የማንነት ጥያቄ ሕገመንግስቱና አግባብ ያለው የሀገሪቱን ሕግ ተከትሎ በዴሞክራሲያዊ አግባብ እንዲፈታ እንዲደረግ፣
  4. ማዕከላዊ መንግስት የኤርትራ ጦር ትግራይ ውስጥ የለም ቢልም ሕዝቡና አባሎቻችን በግልጽ የሚመለከቱት ሃቅ መሆኑ አረጋግጠናል፡፡ ይህ ሃይል በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ እየፈጸማቸው ያሉ ጥቃቶች በርካታ በመሆናቸው በተጨማሪ የንብረት ዝርፊያና ውድመት እንደሚያደርስ መረጃዎች እየደረሱን ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ሃይል የደረሱ ጥፋቶች የሚያጣራ ገለልተኛ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን፣ ሃይሉም ቶሎ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ እዲደረግ፣
  5. በጦርነቱ ሒደት የደረሰው ውድመትና ዝርፊያ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አረና አረጋግጦአል፡፡ ውድመቱና ዝርፊያው በህወሓት ቡድን ብቻ የተፈጸመ ሳይሆን በዚህ ጦርነት በተሳተፉ ሁሉም ሃይሎች ጭምር እንደተካሄደ ዜጎቻችን ይናገራሉ፡፡ ስለሆነም የደረሰው ሰብዓዊ ጥቃት በገለልተኛ ኮምሽን ተጣርቶ አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲደረግ፣
  6. በትግራይ የደረሰው ከፍተኛ የሀብትና የንብረትና የመሰረተ ልማት ውድመት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጽያ ሉዐላዊ ግዛት ውስጥ የተፈጸመ በመሆኑ ሁሉን ኢትዮጽያውያን የሚመለከት ነው፡፡ በመሆኑም ለዘላቂው መፍትሔ ሕዝቡ እንዲተባበር፣ ዳግም በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች መሰል ችግሮች እንዳይከሰት የተቻለውን  ድጋፍና ትግል እንዲደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

 

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top