Connect with us

የቴዎድሮስ ራዕይ አይሞትም፡፡ ያለ እንግሊዛውያን የጋፋትን ትንሳኤ እውን የማድረግ ሌላ ምዕራፍ

የቴዎድሮስ ራዕይ አይሞትም፡፡ ያለ እንግሊዛውያን የጋፋትን ትንሳኤ እውን የማድረግ ሌላ ምዕራፍ
ሄኖክ ስዩም

ባህልና ታሪክ

የቴዎድሮስ ራዕይ አይሞትም፡፡ ያለ እንግሊዛውያን የጋፋትን ትንሳኤ እውን የማድረግ ሌላ ምዕራፍ

የቴዎድሮስ ራዕይ አይሞትም፡፡ ያለ እንግሊዛውያን የጋፋትን ትንሳኤ እውን የማድረግ ሌላ ምዕራፍ

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)

የሠይፈ አርእድ ከተማ አታርጅም፡፡ ደብረ ታቦር ድሮ ቀረ የምትባል ከተማ አይደለችም፡፡ ጠወለገች ሲሏት የምታብብ መናገሻ ናት፡፡ ጋፋት ዋልኩ፡፡ እዚያ የአንዲት ታላቅ ሀገር መሪ ታላቂቷ ብሪታንያ ከምትባለው ሀገር እኩል ሀገሩን ማስተካከል ሲፈልግ ምኞቱን የዘራባት መናገሻ፡፡

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለምድሩ ብርቅ አይደለም፡፡ ዙር አምባ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ቤተልሔምም እንዲሁ፤ ደግሞ የተክሌ አቋቋም ተቋም፡፡ እዚህ በትምህርት መላቅ የትውልድ ቅብብል እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡

ያ መናኛ የተባለው ቦታ ዛሬ ሠርግ ቤት መስሏል፡፡ ብዙዎች በህልውናው ቁጭት ደምተው ቆስለው ነበር፡፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስቀድሞ ቀልቡን ጣለ፡፡ ከዚያ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሲተከል ራሱን ከማኅበረሰቡ ታሪክ ጋር አቆራኝቶ ተከለ፡፡ ዶክተር አለማየሁ ይሄንን ቀን ለማምጣት መሠረቱን ጣሉ፡፡ እነሆ ዛሬ ሆነ፡፡

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ደቡብ ጎንደር ዞንና መከላከያ ሚኒስቴር በጋራ ሆነው ጋፋት ላይ ታላቅ ውጥን ወጠኑ፡፡ አንድ ላይ ሊሰሩ አንዱ ቀን ዛሬ ጀመረ፡፡ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ብዙ እንግዶች ታድመዋል፡፡

ጋፋት ድሮ ቀረ የማይባል ቦታ እንደሚሆን ያሳየ ውጥን በህብረት ተፈረመ፡፡ እዚህ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ደጋግሞ የሚናፈቅ ትልቅ ህልም ተወጥኖ ነበር፡፡ የማደግ፣ የመሰልጠን፣ ከፍ የማለት፡፡ ያን አሳካለሁ ያለው ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዳግም ራሱን ለማኅበረሰቡ ሰጠ፡፡

ደማቅ ነበር፡፡ ብዙ መሰናዶዎች ቀርበዋል፡፡ ነገ ብዙውን አጋራችኋለሁ፡፡ አርቲስት ሱራፌል ተካ መድረኩን አደመቀው፡፡ የቴዎድሮስ ራዕይ እውን ይሆን ዘንድ ግዙፍ ሀሳብ ያለው የአብሮነት ስምምነት ተፈረመ፡፡

ጋፋት በብዙ ዘመን ታሪኳ ከመቅደላ ጦርነት በኋላ እንዲህ ደምቃ አታውቅም፡፡ ዛሬ የተረጋገጠው የናፒየር ጦር ከኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ እንዲህ ያለውን ምኞት ጭኖ መውሰድ የማይችል ነው፡፡ ዘመንም እንዲሁ ህልምን አያደበዝዝም፡፡

ዛሬ እንግሊዛውያን የሉም፡፡ እነሱን ተስፋ ያደረገና እገዛቸውን የሚሻ ምኞትም አይደለም፡፡ ዛሬ ያሰበውም አደርገዋለሁ ብሎ የተባበረውም ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ የበጌምድር ትንሳኤ እውን የሚሆንበት ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት፤

ቀጥሎ ምን ሆነ ቀጥዬ አጋራችኋለሁ፡፡ ሐሙስ ቢሆንም ቀኑ ደብረ ታቦር ደምቃ ቅዳሜ መስሏል፡፡ ሰንበት የመሰለ የጥምቀትን ድባብ በጎዳናዎቿ ላይ እያየሁ ነው፡፡

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top