Connect with us

“ወደ ገደለው ስንመጣ”

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የፈጠረው ቀውስ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

“ወደ ገደለው ስንመጣ”

“ወደ ገደለው ስንመጣ”

(ሙሼ ሰሙ)

ምርጫው ከሚያጠራልን ነገሮች መካክል አንዱና ወሳኙ ጉዳይ የፖለቲካ ሃይል አሰላለፍን (ርዕዮተ ዓለም አላልኩም) እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡ ማን ከማን ጋር ነበር፣ አሁንስ ማን፣ ምንና ከማን ጋር ይሁን፣ ወሳኝ ጥያቄ ነው። ገና ከጠዋት ምርጫው ሃይ ኮፒውን ከኦሪጅናሉ፣ የሕዝብ ልጅን ከታዘለው፣ ጥገኛውን ከጽኑው፣ ቀባጣሪን ከባለ መርሁ እንደሚለይ ምልክት እያሳየን ነው፡፡

በእርግጥም ከፖለቲካው ውስብስብነት የተነሳ አንዳንዱ  ወዴት እንደሚሄድ ግራ ገብቶት መንታ መንገድ ላይ ቆሟል፡፡ ሌላው ደግሞ በአቋሙ ጸንቶ ምርጫውን በመተጣጠፍ ሳይሆን በመርህ ለማሸነፍ እየተፋለመ ይገኛል፡፡

ደጋግሜ እንዳነሳሁት፣ በየክልሉ በሚኖረው “ምርጫ” በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ገዢው ፓርቲ ያሸንፍ ተቃዋሚው ውጤቱ ከብሔረሰቡ ፓርቲዎች ውጭ ሌላ ሃይል ሳይቀላቀል መቶ ፐርሰንት ብሔር ተኮር እንደሚይሆን ግልጽ ነው፡፡

ምናልባትም ከኢህአዴግ ዘመን በከረረ ደረጃ ብሔረተኝነት፣ ጠባብነትና ትምክህተኝነት በአንድ ሲዋሃዱ ምን ማለት እንደሆን የሚገለጽባቸው የምርጫ ሂደቶችና ውጤቶች ልናይ እንደምንችል እገምታለሁ፡፡

ስለዚህ፣ በየክልሉ የሚካሄደው ምርጫ ውድድር ሳይሆን እንደ ቅርጫ ለየብሔሩ ውክልናን በማከፋፈል ላይ እንደማመሰረት ይገመታል። ፍልሚያው በበረታበት ቦታ፣ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል ያልተጠበቀ የብሔር ኋይሎች የጋራ አሰላለፍ ሊከሰትም ይችላል።

በዚህም ምክንያት “ሕይወት ያለው” ምርጫ የሚጠበቀው አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ የሚኖረው የሃይል አሰላለፍም ሲጨመቅ፣ በሶስት መክፈል ይቻላል።

1) አዲስ አበባ የተነጠቀ መብቷ ተመልሶ እራሷን በራሷ ለማስተዳደር ክልል መሆን አለባት፣ የፈቀደ በእኩልነት ሊኖርባት ይችላል፡፡

2) አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት፤ ሌላው ግን እንደመጤ በሁለተኛ ብሔርነት ሊኖርባት ይችላል፡፡

3) አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት ሁሉም ሊኖርባት ይችላል ነገር ግን ኦሮሚያ ደግሞ፣ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ማግኝት አለባት የሚሉ ናቸው፡፡

ከዚህ ውጭ ሶስቱንም አስተሳሰቦች አደባልቀው በተለያየ ጊዜ የተለያየ አቋም የሚያራምዱ ሃይሎች አሉ፡፡

እንግዲህ አዲስ አበቤ ምርጫው ቀርቦልሃል፤ አዲስ አበቤ ምረጥ እልሃለሁ።

በነገራችን ላይ በኋይል አሰላለፍ መዛባት የምንመርጠው ከጠፋ፣ ተመዝግቦ አለመምረጥም አማራጭ ነው። ተመዝግቦ ባለመምረጥ የመራጩን ውጤቱን ከ50 % በታች በማድረግ ምርጫው( null and void) እንዲሰረዝ ማድረግ ይቻላል።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top