Connect with us

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የምሁራን ፎረም ሊቋቋም ነው

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የምሁራን ፎረም ሊቋቋም ነው
አብመድ

ዜና

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የምሁራን ፎረም ሊቋቋም ነው

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የምሁራን ፎረም ሊቋቋም ነው

 ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የምሁራን ፎረም ሊቋቋም መሆኑን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በጽሕፈት ቤቱ የዲያስፖራ ተሳትፎ የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር  አቶ ሔኖክ አለማየሁ እንደተናገሩት፤ የምሁራኑን ፎረም ለማቋቋም የታሰበው ምሁራኑ ለሀገራቸው የሚያደርጉትን አስተዋጾኦ ለማሳደግ ነው።

ምሁራኑ ገንዘብ በማዋጣት፣ የሕዝብ ለሕዝብ ሥራ በመሥራትና በተወሰነ መልኩ የህዳሴው ግድብ ላይ ድርድር በመሳተፍ አስተዋጾኦ ቢያደርጉም ከሌሎች ሀገራት አንጻር ሲታይ ተሳትፏቸው አነስተኛ ነው።

ኢትዮጵያዊያን ምሁራኑ ለምን እንደ ግብጽና ሱዳን ምሁራን በንቃት አይሳተፉም? ብለን ስንጠይቅ ዋናው ችግር ተደራጅተው አለመገኘታቸው መሆኑን ተረድተናል ሲሉም ነው የፎረሙን መቋቋም አስፈላጊነት ያስረዱት።

እንደ አቶ ሔኖክ ገለጻ፤ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል፡፡ ከሳምንት በኋላ ደግሞ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይጀመራል ተብሏል፡፡

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጋር በመሆን ፎረሙ በይፋ እንዲቋቋም እንደሚደረግ ኢትዮ ፕረስ ዘግቧል፡፡

ፎረሙ ከተቋቋመ በኃላ ምሁራን ልዩ ልዩ ሥራዎችን ይሠራሉ ተብሎ ይጠበቃል ያሉት አቶ ሔኖክ፤ በተለይም ደግሞ ፎረሙ በዩኒቨርሲቲዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ስለሚኖረው ምሁራኑ በቀላሉ ለሀገራቸውና ለታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች አስተዋጽኦ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው አስረድተዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጅክት ጥናትና ምርምር የሚካሄድበት ቦታ በማድረግ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ሊሠራበት ይገባል ያሉት ዳይሬክተሩ የጽሕፈት ቤቱ ሥራ ፎረሙ እንዲቋቋም ማመቻቸት መሆኑን ገልጸዋል።(አብመድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top