Connect with us

ያስተዛዝባል!!

ያስተዛዝባል!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ያስተዛዝባል!!

ያስተዛዝባል!!

(ዶ/ር አለማየሁ አረዳ)

በትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ስም የተሰባሰበ አካል መቋሌ ላይ ተሰብስቦ በመወያየት በትግራይ ስላለው ሁኔታ ባወጣው መግለጫ በአካባቢው ተፈጽሟል ስለሚለው ግፍ ሲዘረዝር አንድም ጊዜ

በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ ስለተፈፀመው ግፍ አላወሳም። በመብራትና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ላይ ስለደረሰው ጉዳት ሲዘረዝር መሠረተ ልማቶቹን ማን እንዳወደማቸው እንኳ አልገለፀም።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ ገብቶ እንዲያወያይ ሲጠይቅ ማን ከማን ጋር እንደሚወያይ አልገለፀም።

ምናልባት አሁንም ልብሰ ተክሆኖ አልብሰው በየገዳሙ የደበቋቸው ካሉ ይንገሩንና ይዘዋቸው ይቅረቡ። ለነገሩ መግለጫቸው በሕወአት ቅኝት የተፈበረከ መሆኑን ለማስተዋል ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግሞ። አፈ ሕወአቶች በቋንቋቸው ይታወቃሉና መግለጫቸው ብዙም ስሜት አይሠጥ!

እንደ እውነቱ ከሆነ ተሰባስባችሁ በመወያየት ለችግሩ መፍትሔ ይፈለግ ማለታችሁ ተገቢ ነው የሚጠበቅም ነው። ግን ሚዛናዊ ብትሆኑ ለናንተም ይጠቅም ነበር። ትከበሩም ትደመጡም ነበር። በትግራይ ጉዳይ እውነቱን ለመናገር ኢትዮጵያውያን ሠልችተዋል። በሕወአት መንገድ ከእንግዲህ ትግራይ ሠላም ታገኛለች ብሎ የሚያስብ ካላ ገና ትኩስ እንቅልፍ ላይ ያለ ብቻ ነው የሚሆነው። ብታምኑም ባታምኑም አብቅቷል! ወሬ ቀይሩ!!

ለትግራይ የሚደርስላት ወገኗ የኢትይጵያ ሕዝብ ብቻ ነው!!

ዓለም አቀፍ የሚባል ረጂ ሃይል የለም!!

ድርጊታችሁ ሁሉ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻችሁ ጋር ሆድ እንዳያባብሳችሁ አስቡበት!!

በሕወሓት ዘመን የመቀሌ ኮበሌ ቢማርም ባይማርም አዲስ አበባ ሲመጣ ” ግሪን ካርድ!” ወጣለት ይባል ነበር። እሱ ቀረ!

ከእንግዲህ የትግራይ ልሂቅ የበላይነት በኢትዮጵያ አይሠፍንም!!አርፋችሁ ክልላችሁን አልሙ።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top