Connect with us

ዘይት ያከማቸው ታውቋል~ አፍሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር

ዘይት ያከማቸው ታውቋል~ አፍሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር
አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት

ዜና

ዘይት ያከማቸው ታውቋል~ አፍሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር

ዘይት ያከማቸው ታውቋል~ አፍሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች የአፍሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ያደረገው ድርጊት ኃላፊነት የጎደለውና በዜጎች ላይ የተቃጣ ፍፁም ህገ-ወጥነት በመሆኑ መንግስት ተገቢውን ቅጣት ሊሠጠው ይገባል ሲሉ ጠየቁ።

 በቁጥጥር ስር የዋለው ንብረትነቱ የአፍሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሆነው የምግብ  ዘይት  በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ ጎን  አፍሪካ ኃ/የተ/የግ /ማህበርና የሮዛ  ዳቦ ባለቤት  2 ሚሊዮን ጄሪካን  ፓልም የምግብ ዘይት በአንድ መጋዘን ውስጥ አከማችቶ መገኘቱና ከአካባቢው በደረሰ  የህዝብ ጥቆማ የፌዴራል ፖሊስ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ  አስተዳደር  በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። 

ነዋሪው በተለያዩ ጊዜያት ለወረዳቸው እና ለክፍለ ከተማው ሲያሳውቁና ሲጠይቁ መቆየታቸውን እና አቅርቦት በማጠሩ በተፈጠረው ከዋጋ ውድነት የተነሣ መንግስትን ሲያማርሩ መቆየታቸውን ገልፀው ወደ አከፋፋይ ድርጅቱ አፍሪካ ሃ/የተ/የግ /ማህበር በመሄድ ቢጠይቁም ያገኙት የነበረው መልስ የውጭ ምንዛሪ ስላጣን መግዛት አልቻልንም፤ ከወደብ አልተነሣም፤ መንግስት ሁኔታዎችን አላመቻቸልንም የሚል እንደ ነበር ገልፀዋል።

ሆኖም ግን በድርጅቱ መጋዘን የፓልም ዘይት ሲወርድና ሲራገፍ፤ እንዲሁም ከመጋዘኑ በአሳቻ ሰዓት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተጫነ ሲጋዝ  በተከታታይ ማየታቸውንና ድርጊቱ አግባብ አለመሆኑን በመረዳት ለክፍለ ከተማው መጠቆማቸውን ገልፀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋሪካ ሃ/የተ/የግ/ማህበር ለንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የኢኒስፔክሽን እና ርጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት በቀን 01/06/2013 ከላከው ሪፖርት መረዳት እንደሚቻለው ድርጅቱ በጥር ወር ብቻ በአቃቂ ቃሊቲ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ባጠቃላይ 1,846,532 ሊትር ፓልም ዘይት ማከፋፈሉን እና በመጋዘኑ የሚገኘው 14,003 ሊትር ብቻ በመሆኑ 3,552,376 ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት ወደ አገር ውሥጥ ለማስገባት እንዲፈቀድለት መጠየቁን ያሳያል፡፡

ይህ አፍሪካ ሃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለው ድርጅት የኑሮ ውድነትን ለማቃለል እና በፍጆታ እቃዎች ላይ የሚታየውን የአቅርቦት እጥረት ለማቃለል መንግስት ባመቻቸው እድል በመጠቀም ሸማቹን ማህበረሰብ ማገልገል ሲገባው በገበያው ሰው ሰራሽ እጥረት እንዲፈጠር ብሎም የዋጋ ንረቱ እንዲባባስ በማድረጉ ሊጠየቅ ይገባል ብለዋል፡፡

በቀጣይም በክፍለ ከተማው መሰል የፍጆታ እቃዎችን  በመጋዘን የሚያከማቹ ግለሰቦችንና ተቋማትን ለመቆጣጠር  የተደራጀው ልዩ ግብረሀይል  መንግስት በድጎማ የሚያስገባቸውን መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በህገወጥ መንገድ በማከማቸት እና የአቅርቦት እጥረት በመፍጠር  የንግድ ስርዓቱን ለማዛባት በሚንቀሳቀሱ አካላት የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል ።

ህብረተሰቡ ሲያደርግ ለነበረው ክትትልና ጥቆማ ያላቸውን አድናቆት ገልፀው ወደፊትም በየትኛውም አካባቢ  የፍጆታ ሸቀጦችን የሚያከማቹ አካላትን እና ግለሰቦችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥና ማጋለጡን መቀጠል ይገባል ብለዋል።

(አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top