Connect with us

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መልዕክት

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መልዕክት
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ዜና

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መልዕክት

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መልዕክት

መልካም ዕድል ለተወዳዳሪዎች!!

የተከበራችሁ የፓርቲዎች አመራር አባላት፣ የፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች እና በግላችሁ የምትሳተፉ እጩዎች !!!

ዛሬ ለ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ በእጩነት ስትመዘገቡ ወይም እንደ ፓርቲ እጩዎቻችሁን ስታስመዘግቡ ከፊታችን ያለው መንገድ ከፊል ተስፋ ከፊል ስጋትን አዝሎ እንደሚጠብቃችሁ እንደሚጠብቀን ለሁሉም ግልፅ ነገር ይመስለኛል፡፡

ይሁን እና ስጋትን ለመቀነስ ብሎም ወደ መልካም ሁኔታ ለመቀየር የሚያስችለን አቅም እና እድል በየፈርጃችን ይዘን ይህን የጋራ ሙከራችንን በዝለት ሳይሆን በጥንካሬ ልንጀምረው ይገባል እላለሁ፡፡

በቀደሙ ምርጫዎቻችን ባልነበረ ሁኔታ የሂደቱን ዋና ተዋናዮች ማለትም ተፎካካሪዎቹን  ግራ ወይም ቀኝ፣ ትንሽ ወይም ትልቅ፣ አገራዊ ወይስ ክልላዊ ሳይል፣ በጥረታቸው ሊያግዝ እና ሳንካቸውን ሊፈታ የተዘጋጀ፣ አቅሙን የጨመረ፣ የገለልተኝነቱን መጠን እና ስፋት ከተፅእኖ ሁሉ የሚከላከል የምርጫ ቦርድ ሂደቱን እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

በፍትሃዊነት በተቃኘ በጎ ሀሳብ  ሳይሆን በሸፍጥ፣ ሌላውን በማክበር ሳይሆን ማንኛውንም መንገድ ተጠቅሞ በእንፃሩ የቆመውን በማጥፋት ባለመ ሀሳብ፣ የሁሉንም የዜጐችን ሐሳብን የመግለፅ ሰላማዊ ዕድል ሳይሆን ኋላቀር የሆነ ግጭታዊ መስተጋብርን ታሳቢ ያደረገ አቅጣጫን ያሰበ ተወዳዳሪ ቢኖር ይህን ከምርጫ  ፖለቲካ ውጪ የሆነ ስራውን  ለአደባባይ አውጥተው ለሰው አይን እና ጆሮ ሊያደርሱ የሚችሉ በቁጥር ትንሽ የማይባሉ የሚዲያ አውታሮች እንደ አገር ያለን መሆኑም ለተሻለ ሽግግር ወደፊት ለመቀጠል የሚያስችል አንድ በጎ እውነታ ነው፡፡

የሲቪል ማህበራቶቻችንንም አናቂ ይባል ከነበረ የህግ ማእቀፍ  ወጥተው ዜጐችን ስለእውነተኛ ምርጫ ሊያሳውቁ እንዲሁም የምርጫ ሂደታችን ጉበኛ /watchman or watchwomen/ ሆኖ በታዛቢነት ለማገልገል በጣት በሚቆጠሩ ሳይሆን በመቶዎች በሚቆጠሩ አደረጃጀቶቻቸው ላይ መሰናዶአቸውን ለማጠናቀቅ ደፋ ቀና ይላሉ፡፡

የአውሮፓ እና የአሜሪካ ታዛቢዎችም ይህን ለአገራችን ትልቅ ትርጉም ያለውን ኩነት በእንግድነት ሊታዘቡ ከመንግስት ግብዣው ደርሷቸው ከእኛው ጋር የሂደቱ አካል ሊሆኑ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ ነው፡፡

ብዙ ሌሎች የምርጫ ማሻሻያችን ብዙ ጎኖች መጥቀስ ይቻላል። ሆኖም በዚህ እንደ ብርቱካን ሚደቅሳ በማወጣው የመጀመሪያ የፌስ ቡክ መልእክቴ በዝርዝር ላሰለቻችቸሁ አልወደድኩም።

ለማጠቃለል ዛሬ ፓርቲዎች በአገራችን የተለያየ አካባቢ እጩዎችን በማስመዝገብ፥ በእጩነት በመመዝገብ  የምርጫ ዘመቻውን ምዕራፍ ስትከፍቱ ለሂደቱ የሚጠቅም በጎ እሴት ለመጨመር፣ በችግር ፈቺነት በጋራ ለመስራት፣ የፖለቲካ ጥቃትን አሮጌ ባህል እለት እለት ለመግደል ( Old habits die hard ወይም ከክፉ አመል መላቀቅ በቀላሉ አይሆንም የሚለውን ያስቧል)፤ ለዘመናዊ እና ስልጡን ውድድር ራሳችንን ለማደስ፣ ከምንም በላይ የዜጐቻችንን ባለስልጣንነት በማክበር እንዲሆን  እያሳሰበኩ በዚህ አስፈላጊ እና ትልቅ ትርጉም ባለው ሥራ የሁላችንንም አብሮነት እና የእያንዳንዳችንን ድርሻ ሳንረሳ በበጎ መንፈስ የምርጫ ውድድሩን እንጀምር ስል ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

በድጋሚ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያለበትን  ህጋዊ ሀላፊነት እና ግዴታ እንደሚወጣ ፥እየተወጣም እንደሚገኝ አረጋግጥላችኸዋለሁ።

መልካም የምርጫ ዘመን!

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top