Connect with us

የትግራይ ክልል ፖሊሶች የተሀድሶ ስልጠና ወሰዱ

የትግራይ ክልል ፖሊሶች የተሀድሶ ስልጠና ወሰዱ
የፌደራል ፖሊስ

ዜና

የትግራይ ክልል ፖሊሶች የተሀድሶ ስልጠና ወሰዱ

የትግራይ ክልል ፖሊሶች የተሀድሶ ስልጠና ወሰዱ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ የሙያ መስኮች ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ የትግራይ ክልል ተወላጅ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በአጭር ጊዜ የታህድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው የትግራይ ክልል ህዝብ እንዲያገለግሉ ስምሪት ተሰጣቸው፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ህግ የማስከበር ዘመቻ በትግራይ ክልል ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከሌሎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የህግ ማስከበር እና የክልሉን የጸጥታ ተቋማት በማደረጀትና ተቆርጠው የቀሩትን የጁንታው አመራሮችን አድኖ ለፍርድ በማቅረብ ረገድ የክልሉን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ የክልሉ ተወላጅ የፌዴራል ፖሊስ አባላት  ተልእኳቸውን በብቃት እንዲወጡ ስምሪት ተሠቷቸዋል፡፡

ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ በማን አለበኝነት ሀገርን ለማፍረስ ህዝብን ለማተራመስ የሚሰሩ ግለሰቦችንና ቡድኖችን  ካሉበት ድረስ በመከታተል አድኖ በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ሀላፊነት የተጣለበት የፌዴራል ፖሊስ በመሆኑ የትግራይ ክልል ተወላጅ የፖሊስ አባላት  ወደ ክልሉ ህዝብ በመሄድ ሰላም የተጠማውንና ፍትህ የራቀውን የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የጸጥታ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን የሰላም ጥሙን በማርካት የተሰጣቸውን ግዳጅ በሀገራዊ ስሜት እና ተልዕኮ ስምሪት የተጠሰጣቸው መሆኑን የወንጀል መከላከል ዘርፍ የለውጥ ስራዎች ዲቪዥን ሃላፊ ከማንደር ተስፋዬ ምህረት ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በሁሉም ዞኖች እና  ወረዳዎች ሰላምና ጸጥታን ለማስከበር እንዲሁም የእብሪተኛ ቡድኖችን መሪ እና ተላላኪዎችን በማደንና ለህግ በማቅረብ  የተሰማሩ የሀገር መከላኪያና የፌዴራል ፖሊስ የተሠጣቸውን ተልዕኮ በድል እና በጀግንነት እየተወጡ ቢሆንም በማፍያው የጁንታ ቡድን የተመረዘ የሃሳብ ፕሮፖጋንዳ ጦርነት ምክነያት የተጎዱ የክልሉ ህዝቦች በመኖራቸው ወደ ቀድሞው የህይወት መስመር በመመለስ፤ የሰላም አየር እንዲተነፍሱ በማድረግ፤ የሁላችንም ሀላፊነት እንደሆነ በመረዳት ግዳጃችንን በጥንቃቄ እና ትኩረት በተሞላበት  ልንሰራ ይገባል ሲሉ የፌዴራል ፖሊስ የስራ ባልደረባ እና የትግራይ ክልል ጊዚዊ አስተዳደር የጽጥታ ቢሮ ሃላፊ ኮሚሽነር ግርማይ ካህሳይ ከልጸዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አየይዘውም እንደገለጹት ህዝቦችን በማረጋጋት የነገ ማህበራዊ ህይወታቸውን እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲቀጥል ሰላምን በመገንባት በሚተዳደሩበት የሙያ መስክ በማሳተፍ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ያለ ስጋት እንዲቀጥሉ ለማድረግ የትግራይ ክልል ተወላጅ የፌዴራል ፖሊስ  አባላት ከሌሎች የጸጥታ አካላት  ጋር ሆነው በአብሮነት መንፈስ መስራት ይጠበቅባቸዋል  በማለት የጸጥታ ቢሮው ሀላፊው አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሰላምን ለማስከበር እስከ ህይወት መሰዋትነት የተከፈለበት በህወሐት ጁንታ የጥፋት ቡድን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን የትግራይ ህዝብ የሰላም እጦት ችግሮቻቸውን  በፍጥነት በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረጉ ትግሎች ህግ የማስከበር ስራው በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ  መሆኑን በመግለጽና ህብረተሰቡ ያሉበትን ችግሮች በአፍ መፍቻ ቋንቋ ተናጋሪ መመደቡና የችግሮች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከሌሎች አጎራባች ክልል ህዝቦችጋር በወንድማማችንትና አብሮነት መፈንፈስ እንዲቀጥሉና የተበታተነውን የጥፋት ቡድን ማፍያዎችን ከትግራይ ክልል እንዲጸዱ ለማድረግ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የጸጥታ ተቋማት  እና የፍትህ አካላት ጋር  በጋራ እየሰራ  እንዳለ በመግለጽ፤ ስምሪቱ ወቅቱን የጠበቀና ትልቅ ሀላፊነት የተሰጣቸው መሆኑን አንዳንድ የስምሪቱ አስተባባሪ የትግራይ ክልል ተወላጆች ገልጸዋል፡፡(የፌደራል ፖሊስ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top