Connect with us

በሱዳን ጀርባ የተፈናጠጠውን ኃይል የምንደቁስበት ጊዜ እነሆ ደረሰ

በሱዳን ጀርባ የተፈናጠጠውን ኃይል የምንደቁስበት ጊዜ እነሆ ደረሰ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

በሱዳን ጀርባ የተፈናጠጠውን ኃይል የምንደቁስበት ጊዜ እነሆ ደረሰ

በሱዳን ጀርባ የተፈናጠጠውን ኃይል የምንደቁስበት ጊዜ እነሆ ደረሰ

(ጫሊ በላይነህ)

ልብ በል፤ በጎንደር በኩል ሱዳን ድንበር ጥሳ፣ ሰተት ብላ ወደኢትዮጵያ የገባችው ለምን ይመስልሃል? በነፍስ ሔር ህወሓት ሴራ ነው፡፡ ህወሓት በጦርነትና ሀገር በማተራመስ ተመልሳ አራት ኪሎ በአጭር ጊዜ እንደምትገባ እርግጠኛ ነበረች፡፡ የዕቅዷ አጽዳቂ ደግሞ ግብጽ ነበረች፡፡ ህወሓቶችን የግብጾች አይዞህ ባይነት ልባቸውን አሳብጦት ነበር፡፡ በግዙፉ የሰሜን እዝ ጦር ላይ እነነፍስ ሔር ሴኮቱሬ “መብረቃዊ ጥቃት አደረስን” ብለው ሲመጻደቁ የፕሮፖጋንዳ ግባቸው ግልጽ ነበር፡፡ “ትግራይ የጠላቶችዋ መቀበሪያ ትሆናለች” የሚለው ተደጋጋሚ ቀረርቶ ግቡ የመከላከያን ስነልቦና ለመስለብ ያለመ ነበር፡፡ እና ግብጾች ይኸን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ ትርምሱ እንዲቀጥል በውስጥና በውጭ ቅጥረኛ ኃይላት ፊት ለፊት መጥተው እያየናቸው ነው፡፡

የሱዳን ጦር ሰራዊት አንዳንድ ሙሰኛ አመራሮች ከግብጽ የሚጣልላቸውን ፍርፋሪ በመለቃቀም “አሁን ጊዜው ጥሩ ነው፣ አመቺ ነው” ባሉበት ጊዜ በድንበር ይገባኛል ጥያቄ ስም ምስኪን የኢትዮጵያ ገበሬ ላይ ጦር መዝዘው ሉዐላዊነታችንን በጠራራ ጸሐይ ደፈሩ፡፡

ዕቅዱ የተጠናና የተናበበ ነበር፡፡ ህወሓቶች ጥቅምት 24 ቀን ጦርነቱን ሲለኩሱ፣ የግብጽ የውክልና ጦርነት የሚያስፈጽመው የሱዳን ጦር ከአምስት ቀናት በኋላ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድንበራችን ጥሶ ገባ፡፡

የሱዳን ወረራ ዓላማው ግልጽ ነው፡፡ ድንበር ለማስከበር ወረራና ጉልበት አዋጪ አለመሆኑን ሱዳኖች ይስቱታል ተብሎ አይገመትም፡፡ ዓላማው የኢትዮጵያን ጦር ጎትቶ በድንገት ጦርነት ውስጥ መዶልና ህወሓት ላይ የሚደረገውን የሕግ የማስከበር ስራ እንዲላላ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህም ሕወሓቶች ትንፋሽ አግኝተው እንዲያንሰራሩ የታቀደ ግልጽ ማበር ነበር፡፡ በዚህም አጋጣሚ ህወሓት ሀገርን እስከመሸጥ የደረሰ ቅሌትዋ ፍንትው ብሎ እንድናየው እድል አግኝተናል፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ ለሚዲያ ሰዎች ሲናገሩ “ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያለውን ችግር ማጉላት ያልፈለገችው ጉዳዩን ቀጠናዊ ላለማድረግ ነበር” ብለዋል፡፡ በእርግጥም ህወሓት ሮኬት ወደአስመራ ስትተኩስ ብቸኛ ዓላማዋ ጉዳዩን ቀጠናዊ በማድረግና በማወሳሰብ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት መሳብ ነበር፡፡ አሁንም ግብጾች ሱዳናውያንን ከጀርባ እየጋለቡ ወደኢትዮጵያ ድንበር ገስግሰው የገቡት ጦርነቱን ቀጠናዊ በማድረግ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ትኩረት መቀነስ እና ቢቻል ስራውን ማስተጓጎል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

እናም የግብጾች ሴራ ድንበር ከመውረር ሊሻገር ያልቻለው በኢትዮጵያ በኩል ሕጋዊ አካሄዶች ብቻ በመመረጡ ነው፡፡ ዘሎ ወደጦርነት አለመገባቱ የዲፕሎማሲ ዋጋው ከፍተኛ ነው፡፡

በዚህ የተበሳጩት ግብጾች በውክልና ጦርነታቸው አሁንም ወደኢትዮጵያ ድንበር በጣም ዘልቀው እየገቡና ጉዳት እያደረሱም ስለመሆኑ ተሰምቷል፡፡

እንግዲህ ትግእስትም ልክ አለው እንዲሉ ኢትዮጵያ ደጃፍዋ ድረስ የመጣን ወራሪ ቆንጥጣና አስተምራ መመለስን ድሮም የተካነችው ጥበብ ነውና ዛሬም ለመተግበር የምትገደድበት ሰዓት እነሆ ደርሷል፡፡

የግብጽ ፈረሶቹን ሱዳናውያን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድንበር የማስከበር ስራው የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ግዴታ መሆኑን በመረዳት ለአይቀሬው ግዳጅ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top