Connect with us

ፕሮፌሰር ሒሩት ወ/ማርያምን ይቅናዎ እንበላቸው?

ፕሮፌሰር ሒሩት ወ/ማርያምን ይቅናዎ እንበላቸው?
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ፕሮፌሰር ሒሩት ወ/ማርያምን ይቅናዎ እንበላቸው?

ፕሮፌሰር ሒሩት ወ/ማርያምን ይቅናዎ እንበላቸው?

ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ኢትዮጵያን ወክለው የአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት ለመወዳደር ዕጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡ በአሁን ሰዓት በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ በመሆን በማገልገል ላይ ናቸው።ቀደም ሲል በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነት ከ25 ዓመታት ለላቀ ጊዜ ሰርተዋል፡፡ ከለውጡ ወዲህም በተለያዩ የሚኒስትርነት ቦታዎች ተሹመው አገልግለዋል፡፡

ከአዲስ ማለዳ ያገኘነው ዘገባ እንደሚያስረዳው  ሒሩት ወልደማርያም (ፕሮፌሰር) የመጀመሪያ እና ኹለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ልሳን ትምህርት ዘርፍ ይዘዋል። ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ጀርመን አገር ከሚገኘው ኮሎኝ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ የትምህርት መስክ ሠርተዋል። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመመለስ በተማሩበት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍል መምህር፣ ተመራማሪና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። የመሪነት ክሕሎታቸውን በየደረጃው ማስመስከር የቻሉት ፕሮፌሰሯ የዩንቨርሲቲው ምክትል ፕሬዘዳንት እስከመሆን የደረሱ ብቸኛዋ ሴት ናቸው። በዚህም የሥራ ድርሻ ከአምስት ዓመት በላይ አንጋፋውን የትምህርት ተቋም አገልግለዋል።

የመሪነት ብቃታቸውን በየጊዜው እያስመሰከሩ የመጡት ምሁሯ የፌደራል መንግሥቱን የሥራ ኃላፊዎች ቀልብ ይበልጥ መሳብ የጀመሩት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስተዳደር ጊዜ ነበር። ወደ ግብጽ የሚሄደውን የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ሲዋቀር የቡድኑ አባል ሆነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተመረጡ። ብዙም ሳይቆይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔያቸውን በድጋሚ በምሁራን ሲያዋቅሩ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ተደርገው ተሾሙ።

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መንበር ከተቆናጠጡ ጥቂት ሳምንታት በኋላ ካቢኔው እንደገና ሲዋቀር ሒሩት ወልደማሪያም የሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው እንደገና ተሾሙ። በዚህ የኃላፊነት ወንበር እምብዛም ሳይቆዩ አዲስ ወደተቋቋመው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትርነት ተዛውረው ሰርተዋል።

ፕሮፌሰር ሒሩት የሶስት ልጆች እናትም ናቸው፤ ከመደበኛ ስራቸው ጎን የቤተሰብ ኃላፊነት ተሸክመው መቆየታቸው በየትኛውም ዘርፍ ብቃትን እንደሚያላብሳቸው ይታመናል፡፡

እኚህ አንጋፋ ምሁር አሁን ደግሞ ኢትዮጵያን ወክለው ወደአፍሪካ ህብረት እያማተሩ ይገኛሉ፡፡ ይቅናዎ፤ መልካም ዕድል እንበላቸው?!

(ጫሊ በላይነህ)

(መነሻ ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top