የአሁኑ የካርቱም ዘፈን ፤ ”ከሱዳን መጣን ልናያችሁ …” ከሚለው ይለያል፡፡
(እስክንድር ከበደ)
ከሱዳን ዳርፉር የሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ ፤ የሱዳን መንግስት ግፊት እንዲያደርግ ግብጽ አታደርገውም አይባልም፡፡ ሰላም አስከባሪው ከአካባቢው እንዲለቅ የተፈለገው ያለምክንያት አይደለም፡፡ የሰላም አስከባሪው አባላትን በብዛት ያዋጣችው ኢትዮጵያ በመሆኗ፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ስር ቢሆኑም የሱዳንና የግብጽ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መታዘባቸው አይቀርም፡፡
ግብጽ ወታደራዊ ባለሙያዎች ፣ጠበብትና ተዋጊዎች የሱዳንን ”ወታደራዊ ዩኒፎርም”(ህግ ማስከበሩ ዘመቻ መካሰስን እንደመነሻ ወስደን) ለብሰው በዳርፉር ምድርና በሌሎች የሱዳን ስፍራዎች ምድብ (የአየር ኃይልን ጨምሮ ) ከፍተው ኢትዮጵያን ለማጥቃት አያስቡም ማለት አይቻልም፡፡
የሰላም አስከባሪው ሰራዊት ሱዳን ምድር ውስጥ እያለ ግብጽና ሱዳን ሴራቸውን መፈጸም ይከብዳቸዋል፡፡በዳርፉር ብጥብጡ ቢነሳና ሌሎች የሱዳን ኃይሎች በሱዳን መንግስት ፈተና በቢሆኑ በሱዳን ግብዣ የግብጽ ወታደሮች ወደ ዳርፉር ሊገቡም ይችላሉ፡፡
በህግ ማስከበሩ ዘመቻ የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ክልል ገብተዋል በማለት የአረቡ ጸሀፊያንና የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሀን ፍንጭ ለማግኘት ወይም በመላምት የሚጽፉበት ከጀርባው ከበደ ያለ ምክንያት እንዳለው መጠርጠር ያስፈልጋል፡፡ ኤርትራ ኢትዮጵያን አግዛለች በሚል ግብጾች ከሱዳን ጋር ለማበር ጠንካራ ማስረጃ ፍለጋ ይመስላል፡፡
የተ.መ.ድ ሰላም አስከባሪ ከሱዳን መውጣት ለሱዳን መንግስትና ህዝብ የሚፈጥረው በኢኮኖሚም ሆነ የጸጥታ ማስከበር የሚፈጥረው ጫና ይታወቃል፡፡ እ.ኤ.አ በ1967 የተካሄደው የእስራኤል ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የግብጹ ፕሬዚዳንት ጋማል አብዱናስር የመጀመሪያ ጥያቄ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ጦር ከመካከለኛው ምስራቅ እንዲወጣ ነበር፡፡
ግብጽና ሳኡዲአረቢያ የመሩት የገልፍ አገራት በኳታር ላይ እ.ኤ.አ በ2017 ሰኔ ወር ላይ በድንገት የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማአቀብ እንደጣሉ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ኤርትራና ጂቡቲ የሚወዛገቡበትን የራስ ዱሜራ( እኔ ለአትዮጰያም የሚገባ ብዬ የማስበው ስትራቴጂክ ቦታ) የኳታር 800 ወታደሮች ለቀው በመውጣታቸው ኤርትራ ወዲያው ተቆጣጥረውታል፡፡
ኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማአቀብ ለማስነሳት በሚያደርጉት ጥረት ጂቡቲ ኤርትራ ራስ ዱሜራን ይዛብኛለች ብለ እሪ ማለቷ ይታወሳል፡፡ ይሄኔ አብይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ዶክተር ወርቅነህና የሱማሊያን ልኡካን ወደ ጂቡቲ ልከው የጂቡቲን ተቃውሞ አለዝበዋል፡፡ እናም ኤርትራ ማእቀብ ተነሳላት፡፡
ሰሞኑን ሳኡዲአረቢያ መራሹ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ከኳታር ጋር እርቅ ለማድረግ የተለሳለሰ አቋም መያዛቸው ተስምቷል፡፡ የግብጽ አንድ እርምጃ በብዙ መለኪያዎች የምንመዝንበት ጊዜ ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ካይሮ የአባይን ወንዝ ጉዳይ የቼዥ ጫዋታ ካደረገችው ቆይታለች፡፡ እያንዳንዱ ጠጠር የምትገፋው በጥንቃቄ ነው፡፡ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል፡፡
ከሱዳን ጋር አብረን በሱዳንኛ ድሮም ዘፍነናል፡፡ ”ከሱዳን መጣን ልናያችሁ …” በአረብኛ ቅላጼ አማርኛ የዘፈነው ዘፋኛቸውን የአሁኖቹ ያውቁታል ብለን ከተኛን ሀገርን አስይዘን ከመቆመር አይተናነስም፡፡