Connect with us

ወይ ትራምኘ?!..ወይ አሜሪካ?!

ይ ትራምኘ?!..ወይ አሜሪካ?!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ወይ ትራምኘ?!..ወይ አሜሪካ?!

ወይ ትራምኘ?!..ወይ አሜሪካ?!

የዩናይትድ ስቴትስ ተሰናባቹ ኘረዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገርኛ አባባል “እፍርታም” ናቸው። ገና በድምፅ የመበለጥ ምልክት ማየት ሲጀምሩ ፈጥነው ምርጫው እየተጭበረበረ ስለመሆኑ ለመናገር የቀደማቸው አልነበረም። በተለያዩ ግዛቶች ያቀረቧቸው አቤቱታዎችም መልካም ምላሽ አላመጡላቸውም።

ዛሬም ከነጩ ቤተመንግስት ሊሰናበቱ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ዕድሜ ላይ ሆነውም ስለምርጫ መጭበርበር እና ህጋዊ ኘረዝደንት እሳቸው ስለመሆናቸው መደስኮርን አላቆሙም።

እናም ትላንት ማምሻው በዋሽንግተን ዲሲ የታየው የትራምኘ ደጋፊዎች አመፅ የትራምኘ የተጠራቀመ ቅስቀሳ ውጤታቸው ነው ማለት ይቻላል።

የትራምኘ ደጋፊዎች ትላንት የአሜሪካ ተወካዮች ም/ቤትና ሴኒቱ በጋራ ጆ ባይደን በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ  አሸናፊ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ የምርጫ ኮሌጅ ድምጾችን በመቁጠር እና በማረጋጋጥ ላይ እያሉ፤  የአሜሪካ ም/ቤትን ጥሰው የገቡ ቢሆንም በመጨረሻ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ ወደመጡበት ተመልሰዋል።

ተመራጩ ኘረዝደንት ጆ ባይደን ድርጊቱን ያወገዙ ሲሆን ኘረዝደንት ትራምኘ ግን “ምንም እንኳን ምርጫውን ያሸነፍን ቢሆንም…” ወደቤታችሁ ግቡ የሚል ንግግር በማድረግ በእሳቱ ላይ ቤንዚን አርክፍክፈዋል።

ይኸንን ተከትሎም እነቲውተር፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም የትራምኘን አካውንት በጊዜያዊነት እስከማገድ የደረሰ እርምጃ ለመውሰድ ተገድደዋል።

በተቃውሞው ምክንያት የቆጠራ ሒደቱ ከተቋረጠ በኋላ እንደገና ተጀምሯል።

ከአመፃው በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኃላ የሰዓት እላፊ ታውጇል።

በአመፃው በአንዳንድ ሰልፈኞች እና የህግ አስከባሪ አካላት ላይ ጉዳት የደረሰ መሆኑ ሲረጋገጥ እስካሁን አንዲት ሴት መሞቷ ተረጋግጧል።

ክስተቱ በአሜሪካ የምርጫ ታሪክ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።

(ጫሊ በላይነህ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top