Connect with us

አባይ ወልዱ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አባይ ወልዱ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ በቁጥጥር ስር ዋሉ
አቶ አባይ ወልዱ እና ዶ/ር አብርሀም ተከስተ

ህግና ስርዓት

አባይ ወልዱ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አባይ ወልዱ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ በቁጥጥር ስር ዋሉ

~ሌሎችም ሹማምንት ይገኙበታል፣

አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያደረጉ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለፀ።

ዋነኛ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከአገር መከላከያ ሠራዊቱን በማስከዳት ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩና በጦርነቱ ከሠራዊቱ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና የግል ጥበቃዎቻቸው ላይ እርምጃ መወሰዱንም የመከላከያ ሠራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።

ብርጋዴል ጄኔራሉ ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል የፍተሻ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም ተገልጿል።

ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ እንደገለፁት የቀድምው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የጁንታው ሲቪል አመራሮች እንዲሁም ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ አመራሮችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-

1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረና አሁን የጁንታው ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረ

2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበረና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ጁንታውን የተቀላቀለ

3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች

4ኛ – ሁለት መስመራዊ መኮንኖች

5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ጁንታው የተቀላቀለ ናቸው።

በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ገልፀዋል።

እነዚህም

1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ

2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ

3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ

4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ

5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ

6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ

7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሁለት ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ መሆናቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ  ለኢዜአ ገልፀዋል።

ፎቶ:-አቶ አባይ ወልዱ እና ዶ/ር አብርሀም ተከስተ

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top