Connect with us

እውነትም ግን ቅዱስ ላሊበላ እንደምን አድርጎ ሠራው?

እናቶቻችን ገና ሲያዮት ”እንደምን አድርጎ ሰራው?” አሉ፤ ዓለም ዛሬም ድረስ ይሄን ይጠይቃል፡፡ እውነትም ግን ቅዱስ ላሊበላ እንደምን አድርጎ ሠራው?
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

እውነትም ግን ቅዱስ ላሊበላ እንደምን አድርጎ ሠራው?

እናቶቻችን ገና ሲያዮት ”እንደምን አድርጎ ሰራው?” አሉ፤ ዓለም ዛሬም ድረስ ይሄን ይጠይቃል፡፡ እውነትም ግን ቅዱስ ላሊበላ እንደምን አድርጎ ሠራው?

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የዓለም ቅርስ ስለሆነው የላሊበላ ውቅር ቤተ ክርስቲያን እንደምን ተሰራ የሚለውን ጥያቄ እያነሳ የኩራታችንን ቱሩፋት እንዲህ ተርኮታል፡፡)

ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

እሱ ንጉሥ ነው ግን ደግሞ ቅዱስ፡፡ ለዓለም ደግሞ ዛሬም ድረስ እንቆቅልሽ የሆነ ጥበብን ያኖረ ኢትዮጵያዊ፡፡ የላሊበላ አባቶች የላሊበላን ቅርስ ዩኔስኮ የመዘገበው ጠይቀነው ሳይሆን ጠይቆን ነው ሲሉ በአባታቸው በታላቁ ንጉሥ ሥራ ዛሬም አንገታቸው ቀና ብሎ እንደሚኖር ማሳያ ነው፡፡

እናቶቻችን ገና ሲያዮት ምንም ማለት አልቻሉም ነበር፡፡ ደግሞስ ምን ይባላል፡፡ ቅዱሱንና ንጉሡን ትተው ወደ ሰማይ ቀና አሉ፡፡ ከዚያም የሰማዩን አምላክ መልስ ይሰጣቸው ዘንድ ጠየቁት ”ግን እንደምን አድርጎ ሰራው?”ሲሉ፤ ይሄን ጥያቄ ሺህ አመት ሞልቶታል፤ መልስ የለውም፡፡

የዓለም ሊቅ መጥቶ ብዙ አጥንቶ ብዙ ፈትሾ የእናቶቻችንን ጥያቄ ይደግመዋል፡፡ ”ግን እንደምን አድርጎ ሰራው?” ሲል፡፡ ወደ ሰማይ መውጣት ጥበብ ሆኖ ባቢሎን እግዜርን ሊነካ ግንብ ሲክብ ቅዱስ ላሊበላ ግን ወደ ምድር ምሶ በጥበብ ከእግዜር በትህትና የተደበቀ ቅዱስ ሆነ፡፡ እናም የቅዱስም የንጉሥም ሥራዎች ያስከበሯቸው ህዝቦች ሆነን፡፡

የመልከአ ላሊበላ ጸሐፊ ገና ከዛሬ ስምንት መቶ ዓመት በፊት ደብረ ሮሐ እንዲህ የሰው አጀብ የማይለያት እንደምትሆን ተንብዮልን ነበር፡፡ ዓለም ይሄንን ድንቅ ሥራ ለመመልከት ከያለበት እንደሚመጣም ነግሮናል፡፡ እነሆ እየመጣም ነው፡፡

ላስታ በየዓመቱ በዚህ ሰዓት ይሄንን አያለሁ ያለ የዓለም ጎብኚ ይጎርፋል፡፡ የሀገሬ ሰው ደግሞ ቅዱሱንም ንጉሡንም ሊያነግስ የፈጣሪውን መወለድ ሊያበስር እንደ ሰብዓ ሰገል ሩቅ ተጉዞ ይመጣል፡፡

የገድለ ላሊበላ ጸሐፊን ሀሳብ እጋራለሁ፡፡ እንዲህ ነበር ያለው፤ “የእነዚህን አብያተ ክርስቲያናት ሥራ መናገር በምን አንደበት እንችላለን?”

እውነት ነው፡፡ አይቻልም፡፡ የሚቻለው ዛሬም መጠየቅ ነው፤ እንደ እናቶቻችን እኛም “እንደምን አድርጎ ሰራው እንላለን?”

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top