Connect with us

የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ~ ስለመተከል ጭፍጨፋ

የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ~ ስለመተከል ጭፍጨፋ
የኢት የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

ዜና

የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ~ ስለመተከል ጭፍጨፋ

የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ~ ስለመተከል ጭፍጨፋ

~ በመተከል ዞን በማንዱራ፣ በዳንጉር፣ በጉባ፣ በደባጤ፣ በቡለን እና በወንበራ ወረዳዎች ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሂዷል፣

~ እስከ ታህሳስ 14/2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከ163 በላይ ዜጎች ሕይወት ሲያልፍ  ከ31ሺ በላይ ዜጎች  ተፈናቅለዋል፣

ከኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት በመተከል ዞን በተከሰተው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋን አስመልክቶ  የተሰጠ መግለጫ (Press Release)

የኢትዮጵያ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ በተሻሻለው የተቋሙ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1142/2011 እና በመገናኛ ብዙሀንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በህግ የተደነገጉ የዜጎች መብቶች እና ጥቅሞች በአስፈፃሚው አካላት መከበራቸውን እንዲሁም የተሻለ የመንግስት አስተዳደርን ለማስገኘት ነባር ሕጎች ወይም አሠራሮች ወይም መመሪያዎች እንዲወጡ ወይም ፖሊሲዎች እንዲቀየሱ የማሳሰብ ስልጣንና ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተክል ዞን እየደረሰ ባለው የዜጎች ጭፍጨፋ፣የንብረት ውድመት እና ከቤት ንብረት መፈናቀልን አስመልክቶ ለምን የክልሉ መንግስት እና የጸጥታ መዋቅር መከላከልና ድርጊቱን ማስቆም አልቻሉም የሚሉ ጉዳዮችን ለመመርመር እና ለማጣራት የጥናትና ቁጥጥር ቡድን የላከ ሲሆን በተደረገው የጥናትናቁጥጥር ስራም በመተከል ዞን በማንዱራ፣ በዳንጉር፣ በጉባ፣ በደባጤ፣ በቡለን እና በወንበራ ወረዳዎች ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ የተካሄደ መሆኑን ለማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን እስከ ታህሳስ 14/2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከ163 በላይ ዜጎች ሕይወት ያለፈ መሆኑን አንዲሁም ከ31ሺ በላይ ዜጎች  መፈናቀላቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡

በወንጀል ድርጊቱም የክልሉ የመንግስት የአስተዳደር አካላት፣ የፓርቲ አመራሮች እና የጸጥታ መዋቅር አካላት የተሳተፉ ስለመሆናቸው እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት  አካላት የነበራቸው ድጋፍና ክትትል በጣም ዝቅተኛ መሆኑንና ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተል የነበረው የኮማንድ ፖስት ከችግሩ ክብደትና ስፋት አንጻር የሰራው የጸጥታ ማስከበር ስራና በአጥፊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ደካማ እንደነበር በተቋሙ የጥናትና ቁጥጥር ቡድኑ ለይቷል፡፡ ስለሆነም ተቋማችን የክልሉ የአስተዳደር አካላት እና የክልሉ የጸጥታ መዋቅር በወንጀል ድርጊቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው እንዳለበት ይገነዘባል፡፡ በመሆኑም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያለ የመንግስት መዋቅር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ቀዳሚ ተግባርና ሃለፊነቱ ተገንዝቦ የዜጎችን ንብረትና ደህንነት በአግባቡ እንዲጠብቅ እና ዳግም ተመሳሳይ ጉዳት እንዳይደርስ በማሳሰብ፡ በዜጎቻችን ላይ የደረሰው የህይዎትና የንብረት መጥፋት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽን ፡ የሚከተሉትን ምክረ ሃሳብ እናቀርባለን፡-

1ኛ. ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በመተከል ዞን ከህብረተሰቡ ተወካዮች እና ከአመራሩ ጋር ተወያይተው ያስቀመጧቸው አቅጣቻዎች በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆኑ @

2ኛ. የሚመለከተው የፌደራል መንግስት በወንጀል ድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የነበሩ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ፣ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድና ለሕዝብ ይፋ እንድደረጉ፡

3ኛ. የፌደራል የፀጥታ መዋቅር አካላት አሁን ባለው ሀገራዊ እና ክልላዊ የፀጥታ ሁኔታ ጫና እንደሚኖርባቸው እንገነዘባለን፡ ስለዚህ ህገ መንግስቱና ህጉ በሚፈቅደው መንገድ ከሁሉም ክልሎች የተቀናጀ የጸጥታ ሀይል በማዋቀር በክልሉ ተሰማርቶ የዜጎችን ህይወትና ንብረት ሊታደግ በሚችልበት ቁመና ላይ እንዲገኝ የፌደራል መንግስት ከውሳኔ እንዲደርስ ምክረ ሃሳብ እናቀርባለን።(የኢት የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top