Connect with us

የዓፄ ዮሐንስ 4ኛ ሙዚየም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገለት ነው

የዓፄ ዮሐንስ 4ኛ ሙዚየም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገለት ነው
ፌደራል ፖሊስ

ባህልና ታሪክ

የዓፄ ዮሐንስ 4ኛ ሙዚየም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገለት ነው

የዓፄ ዮሐንስ 4ኛ ሙዚየም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገለት ነው

 ሀገራችን ኢትዮጵያ የታላላቅ ነገስታት ሀገር ነች፡፡ ነገስታቱ ዓለም የሚደነቅበትን የጀግንነት፣የስልጣኔና ሌሎችንም ተግባራት በመፈጸም ዛሬ ላይ ያሉትን በርካታ ቅርጾችን አስተላልፈው አልፈዋል፡፡

በመቀሌ ከተማ የሚገኘው የአፄ ዮሐንስ 4ኛ ቤተ መንግስት የኢትዮጵያዊያንን ሀያልነት የሚያሳይና በውስጡ ቅንጡ ቁሳቁሶችን የያዘ ነው፡፡ይህንን ድንቅ ቤተ መንግስት (ሙዚየም) በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች በየጊዜ ይጎበኙታል፡፡ በተለይ በቅርበት ያለው የመቀሌና የአካባቢው ህዝብ እንደ አይኑ ብለን የሚያየው ብርቅዬ ሀብቱ ነው፡፡

የአፄ ዮሐንስ 4ኛ ቤተ መንግስት የሀገር ቅርጽ እንደመሆኑ መጠን ለበርካታ ዓመታት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ይጠበቃል፡፡ በውስጡ ያሉ ቁሳቁሶች ውድና መተኪያ የለላቸው በመሆናቸው በአራት አቅጣጫ በቋሚነትና ግቢው ውስጥ ደግሞ በተንቀሳቃሽ (ፓትሮል) ሲጠበቅ ነበር፡፡

የራሱ የሆኔ የቤተ መንግስት አስተዳደር ብኖረውም የደህንነቱ ጉዳይ ሙሉበሙሉ የሚቆጣጠረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ነው፡፡ የአፄ ዮሐንስ 4ኛ ቤተ መንግስት  ምንም ጉዳት ሳይደርስበት እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የቆየ ቢሆንም ከዛ በኋላ የህወሓት ጁንታ ቡድን  በሙዚየሙና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ያደረሰውን ጥቃት ዋና ሳጂን ገብረ እግዛብሔር ዳምጤ እንዲህ ያስታውሳሉ፡፡  

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ፌጥኖ ደራሽ ሰሜን ዳይሬክቶሬት 3ኛ ደቪዥን እንደ ወትረው ሁሉ የተጠናከረ ጥበቃ ላይ ባሉበት ወቅት ጥቅምት 24 ቀን ከሌሊቱ 4፡00 ሰዓት ገደማ በርካታ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ከቀላል እስከ ከባድ መሳርያ ታጥቀው ሙዚየሙን መክበባቸውን አውስተዋል፡፡

በጥበቃ ስራ ላይ የነበረው የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት ቤተ መንግስቱን አላስደፍርም በማለት እስከ ህይወት መስዋትነት በመክፈል ለማትረፍ ቢታገሉም ድርጊቱ በድንገት በመሆኑና በቁጥርም ሆኔ በጦር መሳርያ ዝግጅት ተመጣጣኝ ስላልነበሩ የጁንታው ቡድኑ ክደት በመፈጸም ሰራዊቱን ከጊቢው በማስለቀቅ በሙዚየሙ ውስጥ የነበሩት ወርቅና  ብርን ጨምሮ ሌሎች ጌጣገጦች፣አልባሳት፣ጥንታዊ የጦር መሳርያዎች፣ታቦትና ሌሎች የሀያማኖት መጠቀሚያዎች  ሳይቀሩ ሙሉ በሙሉ መዝረፉን ዋና ሳጂን ገብረ እግዛብሔር ዳምጤ ገልጸዋል፡፡

ለበርካታ ክፍለ ዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ የመጡ ቅርጾችን የህወሓት ጁንታ ቡድኑ የወሰዳቸው ሲሆን ለመዝረፍ ያልቻለውን ደግሞ ያለ ሪህራሄ በማውደም የአሸባሪነት ተግባሩን ፈጽሟል ብለዋል፡፡

ዋና ሳጅን  ገብረ እግዛብሔር ዳምጤ አያይዘውም በዘራፊው ጁንታ ቡድን ጥቃት የደረሰባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት አስቸጋሪ ቀናት በኋላ በእግር ተጉዘው ጎንደር ከተማ ወደሚገኘው ካምፕ በመድረስ በተሻለ ወኔ ዳግም በመደራጀትና ዘመናዊ መሳርያዎችን በመታጠቅ ተመልሰው ወደ መቀሌ ከተማ በማምራት  ለዚህ ጥንታዊ ቤተ መንግስት የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

  በሙዚየሙ የነበሩት ቁሳቁሶች ቢዘረፉም ውጫዊ የህንጻው ገጽታ ከእነ ግርማሞገሱ ዳግመኛ ጥቃት በማያሰጋ ሁኔታ በተሻለ የሰው ሃይል በመጠበቅ ላይ እንደሚገኝም ዋና ሳጅኑ ገልጸዋል፡፡  

(በሙሉጌታ መሀመድ ~ ፌደራል ፖሊስ)

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top