Connect with us

ዛሬ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ጥቂት ነጥቦች

ዛሬ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ጥቂት ነጥቦች
ፕላንና ልማት ኮሚሽን

ዜና

ዛሬ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ጥቂት ነጥቦች

ዛሬ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ጥቂት ነጥቦች

ባለፉት ዓመታት በልማት ዕቅድ ትግበራ የታዩ ክፍተቶችን እንዲሁም የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖች ከግምት በማስገባት በቀጣዮቹ አስር ዓመታት የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳለጥ የሚረዳ እና የተቀመጠውን ኢትየጵያን ‹‹አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት›› የማድረግ ሀገራዊ የልማት ርዕይ ለማሳካት ጉልህ ሚና የሚኖረውን የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ታኅሣሥ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ፀደቋል፡፡

ይህ የልማት ዕቅድ ከሕዝቡ ጋር ሰፊ ምክክር ተደርጎበት የዳበረና መግባባት ተደርሶበት የዜጎች ባለቤትነት የተረጋገጠበት ዕቅድ ሲሆን፣ ሂደቱም ከታች ወደ ላይ እና ከላይ ወደ ታች በሆነ የዕቅድ አዘገጃጀት መንገድን ተከትሎ በዘርፎች ውስጥና በዘርፎች መካከል ትስስር እንዲኖር በማድረግ የተሰናዳ ነው፡፡

የአስር ዓመት የልማት ዕቅዱ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ገበያ-መር የኢኮኖሚ ሥርዓት በመከተል የግል ዘርፉን ጉልህ ሚናና ተሳትፎ በማሳደግ የበለጸገች ሀገር መገንባት፤ የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን በመፍጠር ፈጣንና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብና ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር፤ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ምርታማነት፣ ጥራትንና ተወዳዳሪነትን በማጎልበት የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ማረጋገጥ፣ የማኅበራዊና የመሠረተ ልማት ጥራትንና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ዜጎች የልማቱ ባለቤትና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እና ሰላምና ፍትሕ የሚያረጋግጡ ጠንካራ ሥርዓት በመገንባትና የሕግ የበላይነትንና ሰብዓዊ መብትን በማስከበር የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ የሚሉ ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት፡፡

ይኸው የልማት ዕቅድ ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት እና የጋራ ብልጽግናን፣ የኢኮኖሚ ምርታማነት እና ተወዳዳሪነትን፣ ዘላቂ የዕድገት እና የልማት ፋይናንስን፣ የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት መሪነት፣ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት የሥርዓት ለውጥ እና የልማት ተጠቃሚነት እና ማኅበራዊ አካታችነትን ለማረጋገጥና የፍትሕ ተደራሽነት እና ውጤታማ መልካም አስተዳደርን ማስፈን እንዲሁም ዘላቂ የሰላም ግንባታና ጠንካራ ቀጠናዊ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማረጋገጥ ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎች (strategic pillars) ላይ አተኩሮ የሚሠራ ነው፡፡

ዕቅዱ የት ያደርሳል?

ከ2013 እስከ 2022 ዓ.ም በሚተገበረው ዕቅድ መሠረት ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ  አመታት በአማካይ 10 ነጥብ 2 በመቶ ኢኮኖሚያዊ እድገት ልታስመዘግብ እንደምትችል ታቅዷል።

መሪ እቅዱ ጥራት ያለው እቅድ ማረጋገጥ፣ ምርታማነትን ማሳደግ፣ የዘርፎችን ትስስር ማጠናከር፣ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ማሳተፍና የሴቶችና ሕጻናት እኩል ተሳትፎ እንዲሁም አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባትን ምሰሶ ያደረገ ነው ።

በነዚህ መነሻዎች ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት አማካይ አመታዊ እድገቷ 10 ነጥብ 2 በመቶ ይሆናል ተብሎ ተገምቷል።

በእድገቱ ግብርና 6 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 13 በመቶና የአገልግሎት ዘርፉ 10 ነጥብ 6 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል።

በመሪ እቅዱ መሰረት የዜጎች አማካይ የነፍስ ወከፍ ገቢ በ8 ነጥብ 2 በመቶ የሚያድግ ሲሆን በአስር ዓመቱ መጨረሻ ላይ የአንድ ኢትዮጵያዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ በአማካይ 2 ሺህ 248 ዶላር እንደሚሆንም ተገምቷል።

ከአስር ዓመት በኃላ ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ኢትዮጵያን ቁጥር ወደ 7 በመቶ ዝቅ እንደሚልና የከተማ ስራ አጥነት ምጣኔም 9 በመቶ እንደሚሆን ተናግረዋል።

በኤሌክትሪክ አቅርቦት ረገድም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንደሚሆንና ብሔራዊ ኃይል የማመንጨት አቅምም 21 ነጥብ 1 ጊጋ ባይት ይደርሳል ተብሏል።

በመሪ እቅዱ መሰረት የግብርና ሚና እየቀነሰ ሄዶ ትልቁን ስፍራ የሚይዘው የኢንዳስትሪ ዘርፍ ይሆናልም ተብሏል።(ምነጭ:- ኘላን ኮምሽን እና ኢዜአ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top