Connect with us

ህወሓት ተወገደ፤ ከዚያስ?

ህወሓት ተወገደ፤ ከዚያስ?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ህወሓት ተወገደ፤ ከዚያስ?

ህወሓት ተወገደ፤ ከዚያስ?

(ጫሊ በላይነህ)

መንግስት” ጁንታው” የሚለው ህወሓት በኃይል ተወግዷል፡፡ ትላንት የጠቅላዩ በድንገት መቀሌ መገኘት የህወሓቶችን ሞት ያረጋገጠ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ለያዠ ለገናዥ ያስቸገሩ ጥጋበኞች ላይመለሱ ተሰናብተዋል፡፡ ግን ሰንኮፋቸው  ትግራይ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ብልጽግና ጉያ ውስጥ አሁንም አለ፡፡ ሰንኮፉን ነቅሎ መጣል ከባድ ስራ አሁንም ይቀራል፡፡ ሰንኮፉ ምድነው? በህወሓት ተወልዶ፣ ተኮትኩቶ ያደገ የተበላሸ አመለካካት ተሸካሚ ኃይል በብዛት አለ፡፡ የእኔ መንገድ ብቻ ቅዱስ ነው፣ የሌላው እርኩስ ነው ባይ ጎዶሎ አመለካከት ነው፡፡ እኔ ከሌለሁ ሰርዶ አይብቀል የሚል የስግብግብ ሀሳብ አቀንቃኝነት ነው፡፡የተቃወመን ሁሉ በኃይል ልጨፍልቅ፣ ላሳድ፣ ልርገጥና ብቻዬን ልቦርቅ የሚል ስካር ያልተላቀቀም ሹመኛ እዚህም እዚያም አለ፡፡

ሰዎቹ የት ነው ያሉት? አንዳንዶቹ  ወጀቡ እስኪያልፍ ዝም ብለው ባሉበት አድፍጠዋል፡፡ አንዳንዶቹ በፍጥነት ማሊያ ቀይረው እንደለመዱት “የብልጽግና መንገድ ብቸኛ መዳኛ ነው!” የሚል ስብከትን ወደማቀንቀን ተሸጋግረዋል፡፡ አንዳንዶች የብልጽግናን ጫማ ውስጥ ሆነው ህወሓታዊ መንገድን በስልት ወደማስፈጸም ለመሸጋገር እያማሟቁ ይመስላል፡፡

አዎ! ብዙዎቹ የህወሓቶችሰዎች  ሌቦች፣ ዘራፊዎች ነበሩ፡፡ ግን ብቻቸውን አልነበሩም፤ አባሪ ተባባሪ ነበራቸው፡፡ በየቦታው “የስ ማን” የሚሉ አፋሽ አጎንባሽ ነበሩዋቸው፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ፤ የምርጫ 97 መብረቃዊ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ከወሰዳቸው ክፉ እርምጃዎች  አንዱ አንዳንድ የትግራይ ሰዎችን በኢኮኖሚ ኢምፖወር ማድረግ የሚለው ይገኝበታል፡፡ ይህ ከበታችነት ስሜት የመነጨ የተሳሳተ ስሌት ጥቂት የማይባሉ ግለሰቦችን አቧራቸውን በማራገፍ ወደሚሊየነርነት ተርታ አሰልፏቸዋል፡፡

ያው አንተም ብትሆን አንድ ምስኪን ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኛ እና ወታደር  በራሱ፣ በዘመድ አዝማዱ ስም በአዲስአበባ ከተማ ውስጥ እልል ያለ የፎቅ ክምር ስለመገንባቱ ቢያንስ ደጋግመህ ሰምተሃል፡፡ ደግሞ አሉልህ፤ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ ብሂልን እያቀነቀኑ የህወሓቶችን ዘረፋ አጅበው የየድርሻቸው የዘገኑ አንዳንድ የቀድሞ ኢህአዴጋዊያን የአሁን የብልጽግና ሰዎች፡፡ ከገቢያቸው በላይ ሐብት ማፍራታቸው እንኳን የማያሳፍራቸው ደንዙዞች አሁንም አሉ፡፡

እናም ብልጽግና ህወሓታዊዋንን ከውስጡ መንጥሮ የማራገፍ ከባድ የቤት ስራ የሚጋፈጥበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ በእርግጥም ህወሓት ተሸንፋ ሞታለች.፣ ተቀብራለች ማለት የሚቻለው አደግዳጊው፣ ፍርፋሪ ለቃሚው፣ የጥቅም ባለድርሻው በጥንቃቄ ተለይቶ መመንጠር ሲቻል ብቻ ነው፡፡

ብልጽግና ሆይ ለራስህ ስትል ውስጥህ አጥራ፣ ሰንኮፎችን ነቅለህ ጣልና የብልጽግናህን መንገድ አጥብቅ!!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top