Connect with us

የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ሆይ፤ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የኖረው ጁንታ በመጨረሻም ትግራይን ዘረፈ፡፡ የእጅ አመል አይለቅም፡፡

የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ሆይ፤ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የኖረው ጁንታ በመጨረሻም ትግራይን ዘረፈ፡፡ የእጅ አመል አይለቅም፡፡
FBC

ነፃ ሃሳብ

የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ሆይ፤ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የኖረው ጁንታ በመጨረሻም ትግራይን ዘረፈ፡፡ የእጅ አመል አይለቅም፡፡

የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ሆይ፤ ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የኖረው ጁንታ በመጨረሻም ትግራይን ዘረፈ፡፡ የእጅ አመል አይለቅም፡፡

ከስናፍቅሽ አዲስ

ሰሞኑን የዲጂታል ወያኔ የውጪው ዓለምና ስም ቀያሬ የአዲስ አበባ አርበኞች በማኅበራዊ ሚዲያ ትግራይ በመከላከያ ሠራዊቱ እንደተዘረፈች ለማሳመን ሲደክሙ ይታያል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንኳን በሀገሩ የትም ዓለም ሄዶ የማይታማው በእጅ አመል ነው፡፡ ይልቁንስ በእጅ አመል ስናማው ብቻ ሳይሆን ያደረገውን አረጋግጠን ስንሞግተው የነበረ ጁንታ ተግባሩ ይታወቃል፡፡

የማኅበራዊ ሚዲያው አርበኞች የትግራይ ህዝብ እንደተዘረፈ ሊያሳምኑን ይሞክራሉ በር ሳይቀር ገንጥሎ ወሰደ አልጋ ጫነ ይሉናል፡፡ ቁሳቁስ የገዛውማ ቢሆን ለጁንታው ተገዝቶ እናት ሀገሩን ባፈረሰ ነበር፡፡

በሽሬ የነበረውን ደጀና ሆቴል እንደአልነበር አድርጎት የሸሸው ማን እንደሆነ የሽሬ ህዝብ ይመስክር፤ አክሱም ኤርፖርትን አውድሞ ተራ ቁስ ይዞ የፈረጠጠው ጁንታ ቢያንስ የእቃ መግፊያ ጋሪ ለጦርነት እንደማይጠቅም ጠፍቶት አይደለም፡፡ በመቀሌ ብዙ ዝርፊያዎች በማን እንደተሞከረ ነዋሪው የሚያውቀው እውነት ነው፡፡

የተከበርከው የትግራይ ህዝብ፤ ጁንታው ኢትዮጵያን ሲዘርፍ ነበር፤ ሀገሪቷ በአጥንቷ ቀርታ ባዶ ካዝና አስረክቦ ቂምና ጥላቻ ሊያቃባ መቀሌ ቢገባም ሀገር ሳያጠፋ መጥፊያው እውን ሆነ፡፡ ይሄ ቡድን የእጅ አመል አለበት፤ የማይነቅለው የለም፤ ገበሬውን ከቀዬው ነቅሎ ሀገር ለመበተን የደረሰ ጨካኝ ነበር፡፡ አንደርታን ከመሬቱ እንዴት እንደገፋው እንኳን ለመረዳት መቀሌ መኖር ግድ አይልም፡፡

ጁንታው ሲሮጥ እየዘረፈ መሮጥ ባህሉና ጠባዩ ስለሆነ ከአዲስ አበባ መቀሌ ሲገባ እንዳደረገው ከመቀሌ ሸሽቶ ዋሻ ሲገባና በዱር በገደል ሲበተንም የትግራይን ህዝብ ለመበተን ያገኘውን እየዘረፈ ነው፡፡ እውነቱን እያወቅነው መከላከያ ዘረፈ ብሎ ኡኡ ማለቱ ማን ያርዳ የነበረ ያስብለናልና ውሎ አድሮ ሃቁ ፍንትው ይላል፡፡

ጁንታው የእርዳታ እህል ሸጦ ሰው እንደ ቅጠል እየረገፈ መሳሪያ በመግዛት የስልጣን ጉዞውን እውን ስለማድረግ የሚያስብ ነው፡፡ ታሪኩም የሚነግረን ይሄንን ነው፡፡ ትግራይ ልጆችሽ ነን በሚሉት ዳግም ወድማለች፤ ተዘርፋለች፡፡ ትግራይ ጠላትሽ ተብላ በተቀሰቀሰችው ዳግም ትሰራለች፡፡ ድል ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት፤

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top