Connect with us

‹‹በትምክህት የደነደነ ልብ ሳይሆን በስልጠና የፈረጠመ ጡንቻ ሁሌም ያሸንፋል›› ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ

ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ ይናገራሉ:-
Ethiopian press agency

ነፃ ሃሳብ

‹‹በትምክህት የደነደነ ልብ ሳይሆን በስልጠና የፈረጠመ ጡንቻ ሁሌም ያሸንፋል›› ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ

ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ ይናገራሉ:-

‹‹በትምክህት የደነደነ ልብ ሳይሆን በስልጠና የፈረጠመ ጡንቻ ሁሌም ያሸንፋል›› 

በትምክህት የደነደነ ልብ ሳይሆን በጦረነት እውቀትና በስልጠና የፈረጠመ ጡንቻ ያለው ኢትዮጵያዊነት የገባው ወታደር ሁልጊዜም የድል ባለቤት መሆኑን ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ አስታወቁ።

ብርጋዴር ጀኔራሉ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደተናገሩት፣ የህውሓት ጁንታ ቀደም ሲል ከ15 ዓመታት በላይ ሲዋጉ ጠንካራ የሚገዳደራቸው ወታደር ነበር፤ አሁንም ለሀገሩ የሚዋጋ ጠንካራ አቅም ያለው የመከላከያ ሠራዊታችን የቀደመ ታሪካቸውን እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል።

ድሮም ምንም አቅም ምንም እውቀት ኖራቸው አያውቅም ነበር ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ከሳዬ፣ ባዶ ውሸትና ትምክህት ብቻ በሞላው ልባቸው ወደጦርነት በመግባታቸው የሽንፈትን ፅዋ ለመጨለጥ ተገደዋል ብለዋል። ድሮም ወደ ስልጣን መምጣት የቻሉት የተዋጊነት አቅም ኖሯቸው ሳይሆን በደርግ መንግሥት ስህተትና ድክመት ህዝቡ መሰላቸት እና የሀያላን ሀገር ጣልቃ ገብነት በመጨመሩ እንደነበር ጠቁመዋል። 

በህውሓት ጁንታ አሁን በጠላትነት የተፈረጀው የኢትዮጵያ ህዝብ እያበላ፥ እያጠጣ፥ መንገድ እየመራ ደጀን መሆን ደግፎ ወደስልጣን አወጣው እንጂ በፊትም ወታደራዊ ብቃት እንዳልነበራቸው አስታውቀዋል። ለዚህ ውለታው ህዝቡን በዘር በመከፋፈል ከማጫረስ በስተቀር ምንም ሳይጠቅሙት መኖራቸውን ገልጸዋል።

የህዝብ ዕንባ የመከላከያ ሠራዊቱ ጥንካሬ ከዚህ ቡድን ነፃ ስላወጣን ምስጋና ሊቸረው ይገባል ብለዋል።

በባዶ ጉራ ሙሉ የመከላከያ ሠራዊቱን በቁጥጥራቸው ስር አውለው፤ በጦር መሳሪያና በሹመት ብዛት የሚያሸንፉ መስሏቸው ሲፎክሩ ቆዩ እንጅ ወታደራዊ ብቃት ያለነበራቸው ቡድኖች መሆናቸውን መከላከያ ሠራዊታችን በገልፅ አሳይቷል ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ፣ ለሁሉም ደባና ተንኮል የሚያስከፈለውን ዋጋ በአግባቡ ለመመልከት እንደቻሉ ጠቁመዋል።

የተዋጊያቸውን አቅም ያላገናዘቡት እነዚህ ተንኳሽ ቡድኖች ዘመኑ የቴክኖሎጂ መሆኑን ሳያስተውሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈው ጦር ሠራዊታችን ባሳየው የኃይልና የእውቀት ብልጫ ትምክህተኛውን ለማሸነፍ መቻሉ የሚያኮራ ይበል የሚባል ተግባር መሆኑን አመልክተዋል።

የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን የሚያከብር ህዝብ መሆኑን እዚህ በተገኘሁበት ወቅት ተመልክቻለሁ የሚሉት ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ፣ እንግዳ የሚቀበል ሰው አክባሪ የሆነ ጠንከራ ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ሀገርን እኛ ካላስተዳደርን ይፍረስ ብሎ መዝለል ተገቢ እንዳልሆነም ጠቁመዋል። 

ከአንድ መቶ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያለባት ሀገር ሁሉም ህዝብ ወንበር መያዝ ቢፈልግ የማይችል መሆኑን አስረድቶ ሁሉም በያለበት ሀገርን የማሳደግ ኃላፊነትን ከመወጣት ባለፈ የግድ ልምራ ማለት ፍትሐዊ ያልሆነ ጥያቄ እንደሆነ ገልጸዋል።

የትግራይ ህዝብ ከዚህ በፊትም ታፍኖ የኖረ አሁንም ታፍኖ ነው ያለው ህዝቡ ፤ ህዝቡ በስሙ ተነገደበት እንጂ ምንም ያልተሠራለት ዛሬም ይህ ህዝብ የተራበ የተጠማ እንደሆነ አመልክተዋል። ልጆቹ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የሚማሩ ናቸው። የህውሓት ጁንታ ለፕሮፖጋንዳ የሚያሳዩትን ያህል ሳይሆን በጥልቀት ሲታይ በችግር እንዲኖር ያደረጉት ይህን የተጎዳ ህዝብ በመካስ ይህን ጨዋ ህዝብ ወደ እውነተኛ ማንነቱ መመለስ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ይጠበቃል ብለዋል።(ኢኘድ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top