Connect with us

ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ ለመበተን በስናይፐር ዋና ከተማ ላይ በቀን በ192 ሰው ትገድል ነበር…

ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ ለመበተን በስናይፐር ዋና ከተማ ላይ በቀን በ192 ሰው ትገድል ነበር፤ የለውጥ ኃይሉ ሦስት ሳምንት ጦርነት ገጥሞ አስር ንጹህ ሰው አልሞተበትም፡፡
Photo: Aron_Simeneh

ነፃ ሃሳብ

ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ ለመበተን በስናይፐር ዋና ከተማ ላይ በቀን በ192 ሰው ትገድል ነበር…

ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍ ለመበተን በስናይፐር ዋና ከተማ ላይ በቀን በ192 ሰው ትገድል ነበር፤

የለውጥ ኃይሉ ሦስት ሳምንት ጦርነት ገጥሞ አስር ንጹህ ሰው አልሞተበትም፡፡

☆☆☆

(ከእሱባለው ወልዴ)

ወያኔ ታሪክም ፈጣሪም የሚነፍጋት ትልቅ እድል ለንጹህ መቆርቆር ነው፡፡ ቄጤማ ይዞ ሰልፍ የወጣ ነፍስ ጎዳና ላይ የጣለች አረመኔ ናት፡፡ ኢሬቻን አክብሮ በድምጹ የተቃወማትን ነፍስ የምታረግፍ መቅሰፍት ናት፡፡ 

በ97 ምርጫ ድምጼ ተበላ ብሎ ጎዳና የወጣ የአዲስ አበባ ወጣትን ለመበተን 192 ሰው በስናይፐር የጨፈጨፈች ቡድን ናት፡፡

ህግ የማስከበሩ ዘመቻ ሦስት ሳምንት ሞላው፡፡ አውሮፕላን ደበደበ ተብሎ የተመለከትነው ቅስቀሳ ግን የተፈነከቱ ወጣቶች ናቸው፡፡ በዚህ ጦርነት አስር ንጹህ ሞተ የሚል ሪፖርት አልሰማንም፡፡ ሞራል የለሽ ቡድን ንጹህ ነፍስ ምኑም አይደለችም፡፡ 

አሁን ያለው መንግስት ጁንታ አይደለም፡፡ ለእያንዳንዷ ንጹህ ነፍስ ይጨነቃል፡፡ ይራራል፡፡

ይህ ጦርነት በትግራይ ህዝብ ላይ የተከፈተ ስላልሆነ የትግራይ ህዝብ ለጁንታው ጀርባውን ሰጥቷል፡፡ ያ የኢትዮጵያ ጠላት ከቅንጡ ሆቴሎች ወጥቶ ጉሮኖ ውስጥ ገብቷል፡፡ በልማት ወደ ገፋት ሀገረ ሰላም ራሱን ሊያስመልጥ ዳግም ተንቤን ወርዷል፡፡ ያንን ተንቤንን የገፋ ፖለቲካና ቂሙን እረስቷል፡፡

ጦርነቱ ስለ ንጹሃን የሚጨነቅ ነው፡፡ ጁንታው ግን የንጹህ ነፍስ አለመጥፋትና የትግራይ ህዝብ አለመጨፍጨፉ ቆጭቶታል፡፡ 

ከሐውዜን የተማረው ሰራዊት ዳግም እንዲህ በህዝብ ሞት ድጋፍ የማሰባሰብን ምኞት አምክኖታል፡፡ እጁም ክቡሩም ርቃኑን የቀረው ጁንታ ወደ ናቃት ዋሻ ለመግባት ተንቤን መክተቱን ዛሬ በጠቅላዩ ገለጻ አድምጠናል፡፡

የተንቤን ህዝብ ዳግም ይሞኛል ብዬ አላስብም፡፡ የሌባ ደጀንም አይሆንም፡፡ 

ጁንታው የቁም ሞት የሞተው ኢትዮጵያን የካደ ቀን ነው፡፡ ሀገሩን ዘርፎ፣ ኑሮውን አሙቆ የጭንቅ ቀን ዓይኑን ትግራይ ላይ ጣለ፡፡ ግን ወደቀ እንጂ ትግራይን አልጣለም፡፡ ድል ለኢትዮጵያና ለትግራይ ህዝብ፡፡

Photo credited to #Aron_Simeneh

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top