Connect with us

ድህረ- ትህነግ፥ ኢትዮጵያችን ከባንዳዊ ቡድኖች ፅዱ መሆን ይኖርባታል !!

ድህረ- ትህነግ፥ ኢትዮጵያችን ከባንዳዊ ቡድኖች ፅዱ መሆን ይኖርባታል !!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ድህረ- ትህነግ፥ ኢትዮጵያችን ከባንዳዊ ቡድኖች ፅዱ መሆን ይኖርባታል !!

ድህረ- ትህነግ፥ ኢትዮጵያችን ከባንዳዊ ቡድኖች ፅዱ መሆን ይኖርባታል !!

( ኃይሌ ተስፋዬ )

…………

ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ናት። ታላቅነቷን የምንመሰክረውም እኛ ብቻ ሳንሆን ታሪክ የሚመሰክረው ሃቅ ነው። እኔ እንደምረዳው አብዛኞቻችን ኢትዮጵያን አናውቃትም፤ አወቅናት ካልንም የምናውቃት በርሀቧ፣ በእርዛቷ፣ በድህነቷ እና በጉስቁልናዋ ብቻ ነው።

ይኹንና ኢትዮጵያ ከሁሉ  ቀድማ የዕውቀት ብርሃን ያየች፣ የአሥራ ሦስት ወር ፀጋ ባለቤት ፣ የራሷ የዘመን መለወጫ የምትከተል ፣ ከራሷ አልፋ ስልጣኔን ለዓለም ያስተዋወቀች፣  ከእርሻ እስከ ማረሻ ፣ ከግብርና እስከ ህክምና፣ ከሥርዓተ ጽሕፈት እስከ ሥርዓተ መንግሥት፣ ከዜማ እስከ ፍልስፍና የሁሉም ስልጣኔ እርሾ የኾነች፣ ነፃነቷን ሳታስደፍር ለብዙ ሺህ ዘመናት ታፍራና ተከብራ የኖረች ታላቅ አገር ነች።  

ምንም እንኳ በተለያዩ ዘመናት ይህችን ታላቅ አገር ሊያዋርዱ የሞከሩ የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳ ስብስቦችን በታሪክ ውስጥ የምናውቅ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያዊነት በራሱ ከዓለት የጠነከረ ጽኑ ማንነት በመሆኑ፣ እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ ጠላት የሚሸርበው ሴራ ሁሉ ሲመክን አይተናል።

እርግጥ ነው፥ በዚህች ውድ አገር ላይ የፖለቲካ ቁማር ሲጫወቱ የኖሩና አሁንም ያሉ፣ እንደ ኦነግ “ሸኔ” ዓይነት አድኀሪያን የነበሩ ቢሆንም፣ እንደ የመንፈስ ወንድሙ ትህነግ ግን ህዝብን ሽፋን እና ከለላ፣ ብሄርተኝነትንም እንደ ሸማ ተጀቡኖ/ ተከናንቦ መሠሪ ፍላጎቱን ሲያሳካ የኖረ ቡድን በአገሪቱ ታሪክ ታይቶም፣ ተሰምቶም አይታወቅም።

አሁን ይህ አሸባሪና ከፋፋይ ቡድን በመንግስት ቁርጠኝነት፣ በመከላከያ ሰራዊታችን ጀግንነት፣ በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ብርቱ ክንድ አፈር እየተጫነው ይገኛል። ደግሞም ባንዳዊነት እየሞተ፣ ኢትዮጵያዊነት እያበበ የመምጣቱ ነገር በከፍተኛ ሁኔታ በሁላችን ላይ ተስፋን ጭሯል።

ይኹንና ድህረ- ትህነግ፥ በህዝብ ላይ ብርቱ መከራ ያደረሱ ወንጀለኞችን (Criminals) ለህግ ማቅረብ፣ በሀገሪቱ ላይ የተከሏቸውን የጥላቻ ትርክቶችንና መዋቅሮችን ማፈራረስ፣ ህገ አራዊት የኾነውን ሕገ መንግሥትም በተገቢው ሁኔታ በማሻሻል ፥ በአገራችን ውስጥ ዘላቂ ሰላም፣ ፍትኅ፣ እኩልነት እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማስፈን ይገባል።

ይህ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ፥ እርሷን ለጠላት አሳልፈው ለመሸጥ ከሚዳዳቸው ባንዳዊ ቡድኖች የምትጸዳ ከመሆኑም በላይ፣ ህዝብ በሚመራው መንግስት ላይ ያለው አመኔታ በእጅጉ ይጨምራል ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር !!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top