Connect with us

”መንግስት በትግራይ በጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውስጥ የሶስተኛ ወገን ተሳትፎ አያስፈልግም” አምባሳደር መለሰ አለም

''መንግስት በትግራይ በጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውስጥ የሶስተኛ ወገን ተሳትፎ አያስፈልግም'' አምባሳደር መለሰ አለም
KTN News Kenya

ዜና

”መንግስት በትግራይ በጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውስጥ የሶስተኛ ወገን ተሳትፎ አያስፈልግም” አምባሳደር መለሰ አለም

”መንግስት በትግራይ በጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውስጥ የሶስተኛ ወገን ተሳትፎ አያስፈልግም” አምባሳደር መለሰ አለም

በኬንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር የሆኑት  መለሰ አለም ” የፌዴራል   መንግስት በትግራይ ክልል በጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውስጥ የሶስተኛ ወገን ተሳትፎ አያስፈልግም” ሲሉ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ መንግስት በውስጥ ጉዳዩ ላይ የሌሎች  ሀገራት ጣልቃ ገብነት እንደማያስፈልገው ገልፀው፤ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በዘመቻው ተሳትፋለች  የሚለውን የአንዳንዶች ሀሳብ አጣጥለዋል።

አምባሳደሩ ይህን  ያሉት በኬንያው ኬ ቲ ኤን  ቴሌቪዥን ጣቢያ  ላይ ቀርበው በሀገሪቱ  ወቅታዊ ጉዳዮች ቃለ-ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ነው።

ኢትዮጵያ የሌላ ሀገራት ድጋፍ ሳይታከልበት በመከላከያ ሰራዊቷ  የውስጥ ጉዳይን መፍታት እንደምትችል ገልጸዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ አልፎ  በአፍሪካ ቀንድም ሆነ በመላው አፍሪካ  ሰላም እና ጸጥታን በማስፈን ታላቅ ስም ያለው ሰራዊት  እንደሆነም ጠቅሰዋል።

መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻውን በትግራይ  የጀመረበትን ሁኔታ ሲገልጹ፤ጁንታው የህወሃት ቡድን ከ20 አመታት በላይ  ክልሉን ሲጠብቅ ፤ህዝብን በልማት ሲያገለግል በነበረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሱን ጠቁመዋል።

የህወሃት የጥፋት ቡድን ከስልጣን ከተወገደ በኋላ  ባለፉት ሁለት አመታት   ህግን በጣሰ መልኩ  ሀገር የማተራመሱን ስራ  ሲሰራ መንግስት ከመጠን  በላይ መታገሱን ነው የተናገሩት።

ቡድኑ የመንግስትን ትዕግስት እንደ ድክመት በመቁጠር እንዲሁም  የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ለመቀበል ዝግጁ እንዳልነበረ ገልጸዋል።

ባለፉት 27 አመታት ሀገሪቱን ሲመራ የነበረው የህወሃት ቡድን የመጣውን ለውጥ  ለማደናቀፍ ፤ ከሌሎች የታጠቁ ቡድኖች ጋር በመሆን የሀገሪቱን ጸጥታ ሲያውክ ነበር።

መንግስት ሀገራዊ ምርጫው በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ክስተት ምክንያት እንዲራዘም ቢያደርግም ቡድኑ  ይህን ባለመቀበል ህገወጥ ምርጫ ማካሄዱን  በቃለ መልልሳቸው ወቅት ገልጸዋል።

የቡድኑን የሴራ እንቅስቃሴ  ለመቀልበስ መንግስት በትግራይ ክልል የጀመረው የህግ ማስከበር ስራ፤የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የትግራይን  ዜጎች ከጁንታው ነጻ ለማውጣት ያለመ ነው ብለዋል።

አምባሳደር መለሰ አለም ህወሃት ያሰማራቸው ታማኝ የልዩ ሀይል እና ሚሊሻ አባላቱ  በማይካድራ በንጹን  ዜጎች ላይ  አሰቃቂ ግድያ ስለመፈጸማቸው ተናግረዋል።

ይህን አሰቃቂ የንጹን ግድያ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጭምር ማረጋገጣቸውን ለኬቲ ኤን ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል።

በግጭቱ አካባቢያቸውን  ለቀው ወደ ሱዳን ለተሰደዱ ወገኖች  የሰብዓዊ  ድጋፍ ለማድረግ  እና መልሶ ለማቋቋም የባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ኮሚቴ ወደ ስራ መግባቱንም ነው የገለፁት።

ከህወሃት ጋር የተጀመረው ህግን የማስከበር ስራ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ  በምታበረክተው ከፍተኛ የሰላም እና ጸጥታ  ሚና ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም ብለዋል።

በትግራይ የተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ  የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ  የገለፁት አምባሳደሩ፤በዚህም ጁንታውን የህወሃት ቡድን ለህግ የማቅረብ ተግባር ነው ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን  ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በርካታ የሪፎርም ስራዎች  በሀገሪቱ  መተግበራቸውንም ገልጸዋል።

ከእነዚህም መካከል ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ፤የኢኮኖሚ ማሻሻያ፤የፖለቲካ ምህዳር ከማስፋት አንጻር እና  በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ መደረጉን አምባሳደር መለሰ አለም ተናግረዋል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top