Connect with us

የመንግሥት ፕሮጀክቶች ያለ በቂ ቅደመ ጥናት በጀት እየተመደበላቸው መሆኑን ዋና ኦዲተር አስታወቀ

የመንግሥት ፕሮጀክቶች ያለ በቂ ቅደመ ጥናት በጀት እየተመደበላቸው መሆኑን ዋና ኦዲተር አስታወቀ
ሪፖርተር

ዜና

የመንግሥት ፕሮጀክቶች ያለ በቂ ቅደመ ጥናት በጀት እየተመደበላቸው መሆኑን ዋና ኦዲተር አስታወቀ

የመንግሥት ፕሮጀክቶች ያለ በቂ ቅደመ ጥናት በጀት እየተመደበላቸው መሆኑን ዋና ኦዲተር አስታወቀ

ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን የመንግሥት የልማት ፕሮጀክቶች ከአዋጭነት ጥናት እስከ ተግባራዊነት ያሉትን ቅድመ ሁኔታዎችና የሚያስፈልጉ ጠቅላላ ወጪዎችን በተገቢው ሁኔታ ክትትልና ጥናት ሳያደርግ፣ በጀት እንዲፈቀድላቸው እያደረገ መሆኑን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ።

ሰኞ ኅዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም. የፌዴራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ደቢሶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመሆን፣ የ2013 ዓ.ም በጀት የኦዲት ባለድርሻ አካላት ፎረም መነሻ ዕቅድ ላይ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ አሁንም በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት እያጣችበት ያለው ፕሮጀክቶችን ያለ በቂ ቅድመ ጥናት እንዲጀመሩ መፍቀድ ሊቆምና ሊታረም እንደሚገባ አሳስበዋል።

ያለ በቂ ጥናት የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች ስም ከመጥቀስ የተቆጠቡት ዋና ኦዲተሩ በአገር ደረጃ ሊገነቡ የታሰቡ ትላልቅ የልማት አውታሮችን ከመጀመራቸው በፊትም ሆነ ከተጀመሩ በኋላ እንዴት መሄድ እንዳለባቸው፣  በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የቤተ መንግሥት፣ የእንጦጦና የሸገር ፓርክን ብቻ በማየት ብዙ ልምድ መውሰድ ይቻላል ብለዋል።

 የፕሮጀክት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓቱ በደንብ ሊታይና ሊገመገም እንደሚገባ የገለጹት አቶ ገመቹ፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የግዥ ሥርዓቱ ከሚፈቅደው ውጪ በጨረታ መገዛት  የነበረባቸው ንብረቶች ሕግ በማይፈቅደውና የዋጋ መግለጫ በሌላቸው አሠራሮች የሚደረጉ ግዥዎች፣ በኦዲት ሥራቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ዋና ኦዲተሩ የአንዳንድ የመንግሥት ተቋማትን የመረጃና የሪፖርት ጥራት አስመልክተው ሲናገሩ፣  ‹‹በውሸት ሪፖርት ሥራ ሠርተናል›› ብለው ይዘው ይመጣሉ ብለው፣  ለዚህም መፍትሔ የሚሆን የሪፖርት ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

 ከኦዲት ጋር በተያያዘ ዋና ኦዲተር ገመቹ በከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት ውስጥ የአሠራር ብልሹነቶችን ‹‹መረን የለቀቁ  አሠራሮች›› በማለት ገልጸው፣   በተለይ የትምህርት ተቋማቱ መማር ማስተማሩን ለማገዝ ተብለው በውስጥ ገቢ ሀብት ማመንጨት ሥራ ላይ እንዲሰማሩ በሕግ ተፈቅዶላቸውና የራሳቸው የሆነ ኢንተርፕራይዝ ከመሠረቱ በኋላ ከመንግሥት መደበኛ በጀት ደመወዝ ይከፍላሉ ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ሌሎች ሥራዎችንም በመንግሥት በጀት እንደሚያስፈጽሙና ከድርጅቶቹ የተሰበሰበው ትርፍ የት እንደሚውል አይታወቅም ብለዋል።

አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በሕዝብ ትራንስፖርት ሥራ ተሰማርተው እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ ገመቹ፣ ይኼ አሠራር እንዴትና ማን እንደፈቀደ አይታወቅም ሲሉ አክለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሒደት ላይ እያሉ ወደ ሥራ መግባታቸውን፣ ሁልጊዜም የምንጮኸው ለዚህ ነውና አሁንም መስተካከል አለባቸው፤›› ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በኦዲት ግኝት ያሉ ችግሮችን በተለይም  የመንግሥት ተቋማት ያላቸውን ሀብትና ንብረት  ሥርዓቱን በጠበቀ መንገድ በመመዝገብ አስፈላጊውን ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ያሳሰቡት ዋና ኦዲተሩ፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጄንሲ እነዚህን በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ያሉ ንብረቶች በአግባቡ ተመዝግብው እንዲቀመጡ እያደረገ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።

‹‹በርከት ባሉ የመንግሥት ተቋማት ብዙ የማይታወቁና ያልተመዘገቡ የመንግሥት ንብረቶች አሉ፡፡ በመሆኑም እነዚህን ንብረቶች ለማስወገድም ሆነ ኦዲት ለማድረግ አስቸጋሪ ሆኖብናል፤›› ሲሉ አቶ ገመቹ አስረድተዋል።( ሲሳይ ሳህሉ – ሪፖርተር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top