Connect with us

“የህወሓት ሃይል ላለፉት ሁለት ዓመታት የጥፋት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 

"የህወሓት ሃይል ላለፉት ሁለት ዓመታት የጥፋት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
አዲስ አድማስ

ዜና

“የህወሓት ሃይል ላለፉት ሁለት ዓመታት የጥፋት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 

“የህወሓት ሃይል ላለፉት ሁለት ዓመታት የጥፋት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 

 

ላለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል የህወሃት ሃይል የጥፋት ተግባራት ሲያዘጋጅና ሲፈጽም መቆየቱን የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ የለውጡ አካል ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ህወሓት ከለውጥ ተግባራት ተቃራኒ በመቆም የተለያዩ ቀውሶችን ለመፍጠር ሲዘጋጅና የጥፋት ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱን ተናግረዋል።

“በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ዘር ላይ ተመስርተው ለሚከሰቱ ሰብአዊ ቀውሶች የህወሓት የጀርባ መሪነት አለበት” በማለት አንስተዋል።

“ከቅርቡ እንኳን ብንጀምር መንግስት በጁንታው ሃይል ላይ እርምጃ መውሰድ የጀመረው የህውሓት ሃይል በመከላከያ ሰራዊት ላይ ባደረሰው ጥቃት ነው” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከህወሓት ጋር የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሲጥሩ ቢቆዩም የህውሓት ሃይል ግን በተቃራኒው ቆሞ የግጭትና የጥቃት ተግባራትን ሲዘጋጁና ሲፈጽም እንደነበር ነው ያስረዱት።

“በሺዎች የሚቆጠሩ የጦር መሳሪያዎች በእምነት ተቋማት ውስጥ ሳይቀር መገኛታቸውን ተናግረው ይህም የህወሓት ቡድን ባለፉት ሁለት ዓመታት ሲሰራ የቆየው የጥፋት ተግባር ማሳያ ነው” በማለት ገልጸዋል።

ቡድኑ በማይካድራ ንጹሃንን እየመረጠ አሰቃቂ ግድያ መፈጸሙንም አስታውቀዋል።

“እንደዚህ አይነት አገር የማፍረስ ሁኔታዎች ሲመጡ መንግስት በቀጥታ ሊያደርግ የሚችለው ህግን የማስከበር ተግባር ነው” ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ።

የመከላከያ ሰራዊት ለህዝቡ አስከቀድሞ ማስጠንቀቂያ በመስጠትም ንጹሃን እንዳይጎዱ በከፍተኛ ጥንቃቄ ህግ የማስከበር ዘመቻውን እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።(አዲስ አድማስ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top