Connect with us

የአየር ጥቃት በመቀለ ከተማ መፈጸሙ ተነገረ

የአየር ጥቃት በመቀለ ከተማ መፈጸሙ ተነገረ
Photo: Social media

ዜና

የአየር ጥቃት በመቀለ ከተማ መፈጸሙ ተነገረ

የአየር ጥቃት በመቀለ ከተማ መፈጸሙ ተነገረ

 

ዛሬ ረፋዱ ላይ በትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ መቀሌ ውስጥ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የከተማዋ ነዋሪዎችና የቢቢሲ ዘጋቢ ከስፍራው ገለጹ።

ዘጋቢያችን እንደገለጸው የጦር አውሮፕላን ድምጽ በተሰማበት ጊዜ በነዋሪዎች ዘንድ መደናገጥ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን፤ በሰዎች ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጾ የነበረ ሲሆን፤ የአይን እማኞች ግን አንድ ሰው የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰበት ተናግረዋል።

ጥቃቱ ረፋድ አምስት ሰዓት ገደማ መፈጸሙን ሪፖርተራችን ገልጾ የጥቃቱ ኢላማውም ነባር የከተማዋ ስታድየም የሆነው ባሎኒ እየታባለ በሚጠራው አካባቢ እንደሆነ ዘጋቢያችን ገልጿል።

የክልሉ ቴሌቪዥንም ሰኞ ኅዳር 07/2013 ዓ.ም ረፋድ 04፡45 ላይ ጥቃቱ መፈጸሙን ያረጋገጠ ሲሆን፤ የጥቃቱ ኢላማም በመቀለ ውስጥ በሚገኘው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው እንዳ ጊዮርጊስ የተባለው አካባቢ መሆኑን አመልክቷል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ በተቀሰቀሰው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በትግራይ ልዩ ኃይል መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ውስጥ መንግሥት በተመረጡ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት እንደሚፈጽም አሳውቆ ነበር።

እስካሁን በተደረጉ የአየር ድብደባዎች የወታደራዊ አቅርቦች ማዕከላት ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ ባይቻልም የክልሉ ባለስልጣናት አንድ አውሮፕላን መትተው እንደጣሉ መግለጻቸው ይታወሳል።

በፌደራል መንግሥቱና ትግራይን የሚያስተዳድረው ገዢ ፓርቲ ህወሓት መካከል ለወራት የዘለቀው ውዝግብ በክልሉ በሚገኘው ሠሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ ወደ ወታደራዊ ግጭት መሻገሩ ይታወሳል።

በዚህ ግጭት በምድርና በአየር ከሚደረገው ዘመቻ ባሻገር የትግራይ ኃይሎች ባለፈው አርብና ቅዳሜ በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኙት በባሕር ዳርና ጎንደር ከተሞች እንዲሁም የጎረቤት አገር ኤርትራ መዲና ውስጥ ያሉትን የአየር ማረፊያዎች ኢላማ ያደረጉ የሮኬት ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አረጋግጠዋል።

እስካሁን በተለያዩ አካባቢዎች ጦርነቶች እየተካሄዱ ሲሆን በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው ዛሬ ተፈጸመ በተባለውና አስካሁን በተካሄዱ ግጭቶች የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ አስተማማኝ መረጃ ለማግኘት አዳጋች ሆኗል።(BBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top