Connect with us

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው
Photo: Social media

ዜና

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው

~የልዑካን ቡድኑ ከማንም ጋር ድርድር አያደርግም ተብሏል፣

 

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያካሄደ ነው።

በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት በመክፈት የሀገር ክህደት የፈፀመውና ተከታታይ የህገ መንግሰት ጥሰቶችን ሲፈፅም የከረመው የአክራሪውን የህወሃት ፅንፈኛ ቡድን ለህግ ለማቅረብ፣ የህግ የበላይነትን የማስፈን ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ይኸው ዘመቻ የውስጥ ጉዳያችንን በራሳችን አቅም መልክ ለማስያዝ የሚካሄድ በመሆኑና አክራሪው ሃይል በህግ ስር ከመሆኑ በፊት ምንም አይነት የውጭ ሃይል እንቅስቃሴ ስርዓት አልበኝነትን በማንገስ የሀገራችንን ሰላም የማደፍረስ ውጤት የሚያስከትል መሆኑን መንግስት አቋሙን ግልፅ አድርጓል።

ይህንኑ አቋም በማስረዳት የቀጠናው አገራት መንግስት የጀመረውን ህግና ህገ መንግስት የማጽናት ጥረት እንዲደግፉ ለማስቻል የጠቅላይ ሚንስትሩን መልዕክት የያዘና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ተለያዩ የቀጠናው አገራት ጉብኝት ጀምሯል።

ጉብኝቱ ከስድስት በላይ አገራትን የሚሸፍን መሆኑ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩጋንዳ ለማሸማገል እንዳሰበችና ለዚሁ ሲባል የልዑካን ቡድን እንደሚጓዝ የሚያትትና በኢትዮጵያም ሆነ በዩጋንዳ ያልተሰበና ተቀባይነት የሌለው የሐሰት መረጃ በፅንፈኛው ቡድን ተፈብርኮ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በመሰራጨት ላይ እንዳለ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top