Connect with us

በሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ የደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ከነገ ጀምሮ በኦሮሚያ ይደረጋል

በሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ የደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ከነገ ጀምሮ በኦሮሚያ ይደረጋል
Photo: Social media

ዜና

በሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ የደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ከነገ ጀምሮ በኦሮሚያ ይደረጋል

በሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ የደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ከነገ ጀምሮ በኦሮሚያ ይደረጋል

በመላው ኦሮሚያ ከህዳር ሶስት ጀምሮ ህገ ወጡ የህወሓት ጁንታ ከግብረ አበሩ ኦነግ ሸኔ ጋር በመቀናጀት በሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ እና ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበረሰብ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ÷ ወንጀለኛው የህወሓት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ፈጽሟል ብለዋል፡፡ 

ይህ አሳፋሪ ተግባር በዓለም ታሪክ ከተፈጸሙ እጅግ አሳፋሪ የጦር ወንጀል ታሪኮች ውስጥ ተመዝግቦ ይኖራልም ነው ያሉት፤ የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ይህ የህወሓት እኩይ ድርጊት በእጅጉ እንዳስቆጣው በመጥቀስ፡፡

በመላው የኦሚሮያ ዞኖች፣ ከተሞች እና ወረዳዎችም ሰላማዊ ሰልፎችን ለማድረግ በርካታ ጥያቄዎች በመቅረብ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ሰላማዊ ሰልፎቹም ህገ ወጡ የህወሓት ጁንታ ከግብረ አበሩ ኦነግ ሸኔ ጋር በመቀናጀት በሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡ መጠየቅ፣ ህዝቡ መንግስት ሕግን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ በመደገፍ ለመከላከያ ሰራዊት እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት ለመግለጽ፣

እንዲሁም  የአጥፊው ጁንታ ጥፋት የጥቂት ስግብግቦች ሴራ እንጂ የሰላም ወዳዱን የየትኛውንም ህዝብ ፍላጎት የማይወክል መሆኑን እና በጁንታው በተፈጸመው ጥፋት ምክንያት የኢትዮጵያ አንድነት እንደማይፈርስ የህዝቦች ወንድማማችነት እንደማይናጋና የጁንታውን  ሀገር የማፍረስ ሴራ በቁርጠኝነት ለመታገል ያላቸውን አቋም ለመግለጽ ያለሙ ናቸው ተብሏል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የጸጥታ አካላትም የህዝቡን የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ  ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት አድርገዋልም ብለዋል፡፡

በመሆኑም በኦሮሚያ ክልል ከነገ ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መፈቀዱን ተናግረዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞቹም ከጸጥታ ሀይሎች ጋር በመተባበር ሰልፎቹ በሰላም እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እና ራሳቸውንም ከኮቪድ 19 ስርጭት ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲንቀሳቀሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡(FBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top