Connect with us

ደግሞ የምን ሰልፍ ነው? ኸረ እየተስተዋለ?

ደግሞ የምን ሰልፍ ነው? ኸረ እየተስተዋለ?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ደግሞ የምን ሰልፍ ነው? ኸረ እየተስተዋለ?

ደግሞ የምን ሰልፍ ነው? ኸረ እየተስተዋለ?

(ጫሊ በላይነህ)

መላው ኦሮሚያ ከነገ ጀምሮ ምድር አንቀጥቅጥ የቁጣ ሰልፍ እንደሚደረግ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ የሰልፉ መነሻ ምክንያት ህወሓት በሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ አዘናግቶ የፈጸመው ኢ- ሰብዓዊ ጥቃት ለማውገዝ ነው ተብሏል፡፡

እርግጥ ነው፤ የህወሓት እርምጃ “ኢ- ሰብዓዊ ነው” የሚለው ቃል አይገልጸውም፡፡ እነ ናዚ እንኳን በሕይወት ቢኖሩ የሚቀኑበት የሰይጣን ተግባር ነው፡፡ ይኸም ሆኖ ግን በዚህ በአገር አቀፍ ደረጃ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ባልተረጋገጠበትና እዚህም እዚያም ከህወሓትና ኦነግ ሸኔ ጋር ተያይዞ የጸጥታ መደፍረስ ስጋቶች ጎልተው በሚታዩበት በዚህ ጊዜ ሰልፍ መጥራቱ ጥቅምና ጉዳቱ በሚገባ ተሰልቷል ወይ ብዬ እጠይቃለሁ፡፡

ይኸ ብቻ አይደለም፤ እስካሁን በኦሮሚያ የሚከሰቱ የሰላም መደፍረሶች፣ የሰላማዊ ሰዎች ግድያዎች ጀርባ ያለው ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ብቻ ነው ማለት ራስን ማሞኘት ይሆናል፡፡ ቁጥራቸው ይነስም ይብዛ፤ በራሱ በብልጽግና ውስጥ ከላይ እስከታች የተሰገሰጉ ቅጥረኞችና አፍራሽ ፖለቲከኞች የሴራው ጠንሳሽና ተባባሪዎች መሆናቸውን መካድ አይቻልም፡፡ 

ብልጽግና ራሱን እንኳን ማጽዳት የሚችልበት የተደላደለ የፖለቲካ ምህዳር ባልፈጠረበት፣ አንዳንድ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ይመለከተናል ባይ ግለሰቦች የአመጽ መንገድን በየደቂቃው በሚሰብኩበት  በዚህ ወቅት ሕዝብን አንጋግቶ አደባባይ ማውጣት ምን ዓይነት የፖለቲካ ትርፍ ያስገኛል የሚለው በቅጡ ስለመታየቱ በግሌ መረጃው የለኝም ፡፡ ያለው ካለ ቢያጋራን ደስተኛ ነኝ፡፡ 

በግሌ ግን ይህ የሰልፍ ጥሪ በተቃራኒው የሰላምና የጸጥታ ስጋትን ሊያባብስ፤ ገፋ ካለም ሕዝብን ለጥቃት ሊያጋልጥ የሚችል አደገኛ ውሳኔ ነው እላለሁ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ መዘንጋት የሌለበት  እንደ ህወሓት ያሉ ሴረኛና የሽብር ቡድኖች በውግዘት እንደማይጠፉ ነው፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው ለሽብር እንቅስቃሴያቸው ያልተገባ እውቅና መስጠት እንዳይሆን በብርቱ መጠንቀቅ ይገባል፡፡

እናም በአጭሩ የአደባባይ ሽለላና ቀረርቶ ቢቆየን?…ከድል መልስ እንደርስበታለንና፡፡ እስቲ በጉዳዩ ላይ ሀሳብ ስጡበት?

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top