Connect with us

ጋሞ-ኤዞ በጥበበኞች ምድር ቤተ ጥበብ

ጋሞ-ኤዞ በጥበበኞች ምድር ቤተ ጥበብ
Photo: ሄኖክ ስዩም

ባህልና ታሪክ

ጋሞ-ኤዞ በጥበበኞች ምድር ቤተ ጥበብ

ጋሞ-ኤዞ በጥበበኞች ምድር ቤተ ጥበብ

 

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ጋሞ ደጋማው ምድር ወጥቷል፡፡ የኢትዮጵያውያን ምድር የሚለውን የጋሞ መንደር ቆይታውን ይተርክልናል፡፡ በኤዞ በብሔራዊ ቤተ መጻህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ የመጻሕፍት ድጋፍ ሲደረግ ነበርኩ ያለበትን ትረካ እንጋብዛችሁ፡፡)

ከሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

እንዲህ ላለች ሀገር ስለሚሞቱ ብሔራዊ ጀግኖች ክብር አለኝ፡፡ ሀገር እንደ ድንጉዛው ቀለመ ብዙ ናት፡፡ ያን ቀለም ከነ መልኩ እያየሁት ነው፡፡ ጋሞ ደጋው ምድር፡፡

ኤዞ አዲስ ወረዳ ናት፡፡ ድምቅ ብላለች፡፡ ትንሽ መንደር የነበረችው ከተማ ዛሬ የቆጎታ ወረዳ ዋና መዲና ናት፡፡ ጋሞ መሃል ስሆን ደስ ይለኛል፡፡ ሽማግሌዎቹ ኢትዮጵያ ሳይሉ አይጀምሩም፡፡ ኢትዮጵያ ሳይሉ አይጨርሱም፡፡ 

እዚህ ደጋው ጋሞ ኮረብታ ላይ ሆኖ ስለ ደናክል ሸለቆ ሀገሬ ብሎ የሚጨነቅ፣ ስለ ደጀን የሚመርቅ፣ ስለ አክሱም ክብር የሚሰማው፣ ስለ ጣና የሚደሰት፣ ስለ ባሮ የሚኮራ፣ ስለ አዋሽ ልቡ ከፍ የምትል፤ ስለ ዋቤ ሸበሌ ደህና መሆን የሚቃትት፣ ስለ ኦሞ ሰላም የሚለምን ኢትዮጵያዊ፤ ጋሞ፡፡ኤዞ አሁን ከተማ ሆናለች፡፡ 

የህዝብ ቤተ መጻሕፍቷ ሊመረቅ እንግዳ ሆኜ መጥቻለሁ፡፡ ቤተ መጻሕፍቱ በር ላይ ነን፡፡ የጋሞ አባቶች ልጆቻቸውን አስቀድመው በክብር ተሰይመዋል፡፡ ግሩም የሆነ የጋሞ የባህል ጭፈራ እያየሁ ነው፡፡ እነሆ የኤዞ ዶክተር ታደሰ ወልዴ ቤተ መጻሕፍት ሊመረቅ ነው፡፡ ዶክተር ታደሰ ወልዴ ሁደጋ ናቸው፡፡ የጋሞ የባህል አባት፡፡ 

ሰውዬው ዓለም አቀፋዊ ምሁር ቢሆኑም በአመት ሁለት ጊዜ የጋሞን ደጋ አየር ካልሳቡ ዘመን የማያድሱ ስስ ልብ ያላቸው ባህል አፍቃሪ፤ በእሳቸው ስም በእሳቸው ባድማ የተሰየመውን ቤተ መጻሕፍት ለመመረቅ ታድመዋል፡፡

ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ አትርቀውም፤ ሁሉም ስፍራ የጎደለውን መደርደሪያ ለመሙላት ይባትላል፡፡ እዚህም እንዲሁ የመጻህፍት ስጦታ ይዞ ታድሟል፡፡

አባቶች ሳር ይዘው መረቁ፡፡ ጋሞ ሆነው ከቀዬቸው የሚሻገር ምርቃት፡፡ ኢትዮጵያ ሰላም ትሆን ዘንድ፤ ጠላቷ አንገቱን ይደፋ ዜጎቿ ቀና ይሉ ዘንድ፡፡ ቀጥሎ ቤተ መጻሕፍቱ ተመረቀ፡፡ የጋሞ ባህላዊ ምግብ ቀረበ፡፡ ጋሞ ሰው የሚጠግብ አይመስለውም፡፡ ስስት የሌለበት ግብዣ ቀጠለ፡፡ እኔ ልቤ ወደ ብርብር ሄደ፡፡ እወስዳችኋለሁ፡፡

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top