Connect with us

“መናገር ሳያስቡ፤ ምላጭ መሳብ ሳያልሙ አያዋጣም!”

"መናገር ሳያስቡ፤ ምላጭ መሳብ ሳያልሙ አያዋጣም!"
Photo: Social media

ዜና

“መናገር ሳያስቡ፤ ምላጭ መሳብ ሳያልሙ አያዋጣም!”

“መናገር ሳያስቡ፤ ምላጭ መሳብ ሳያልሙ አያዋጣም!”

 

ተመስገን ጥሩነህ ~ የአማራ ክልል ኘረዝደንት

“አንድ ነገር ከመናገራችን በፊት ስለምንናገረው ጉዳይ ማሰብ እና ማሰላሰል ያስፈልጋል:: ኢትዮዽያ ትልቅ ሀገር ናት:: ትልቅነት መመዘኛው ብዛትም  ይሁን ሀብት ወይም ታሪክ በሁሉም ትልቅነቷን ታሟላለች:: 

ከሁሉም በላይ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ኢ-ፍትሀዊ እና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን ሲያይ ለሌሎች የዓለም ሀገራትም ሳይቀር የብስና ውሀ አቋርጦም ለሌሎች መድህን ለመሆን የሚሞት ህዝብ ያላት ሀገር ነች:: ህዝቧ ልዩነቱንና ብዝሀነቱን እንደ ፀጋ የሚቆጥር ነው:: 

ይሁን እንጅ ስንዴ ውስጥ እንደሚበቅል እንክርዳድ ሁሉ ኢትዮጵያም ትህነግን አፈራች:: አሳፋሪው ታሪክ ደግሞ ከጀግናው: ታሪከኛው እና እንደ ታሪክ  ሰሪነቱና ጀግንነቱ ከማይመጥኑት የትግራይ ህዝብ ውስጥ ትህነግ የሚባል አይኑን በጥሬ ጨው ያጠበ አጭበርባሪ ቡድን መፈጠሩ ነው:: 

ይህ ቡድን ቢያንስ ቢያንስ በሰራው አፀያፊና አሳፋሪ ሀገርን በታማኝነት ያለመምራት ክህደትም  ይሁን ሰውን እንደ ሰው ያለማክበር አረመኔያዊ ተግባር  መፀፀትና ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት:: ግን ዕድሉን መጠቀም ሲገባው የሌቦች፣ ዘራፊዎች፣ አጭበርባሪዎች እና ሌሎች ህገ ወጦች ሁሉ መድህን ነኝ ብሎ አወጀ:: ኢትዮጵያን በመራበት አሳፋሪ ብቃቱ ትግራይን ሊሞክር ዕድሉን አገኘ:: 

የልማት ሳይሆን የስድብ ቃላቶችን ሲያፈላልግ እና በአየር ላይ ሲረጭ ከርሞ ብንን ሲል ምንም የሰራው ተግባር የለም:: እናም ድሮ በምክንያት እና ጉልበቱ ሳይዝልና አንደበቱ ሳይደክም በበረሀ ያካበተውን ነፃ አውጭ ነኝ የትግል ዘዬ ትዝ አለው:: 

ሳያስብ መናገሩ አነሰበትና የኢትዮዽያ ህዝብ ኩራት: የአፍሪካ መድህን እና በዓለም የሚደነቀው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ ሳያልም ምላጭ ሳበ:: አሳዛኝ የቀብር ቦታውንም አዘጋጀ:: እሱም አመድ ጎባ ይባላል:: ውሏችን እጅግ ወርቃማ ነው:: ሰራዊታችን ምንጊዜም ያኮራል ነገም ድሉ ይቀጥላል:: የዚህ አሳፋሪ ቡድን መቋጫው እንደ እምባገነኖቹ እንደ እነ ስም አይጠሬ  ይሆናል::”

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top