Connect with us

በአሶሳ ከተማ በድብቅ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 20 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በአሶሳ ከተማ በድብቅ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 20 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Photo: ኢዜአ

ዜና

በአሶሳ ከተማ በድብቅ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 20 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከህወሃት ጋር ድብቅ ግንኙነት በመፍጠር በአሶሳ ከተማ ጥፋት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ የተጠረጠሩ 20 ግለሰቦች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱላዚዝ መሐመድ አስታወቁ።

ኮሚሽነሩ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ግለሰቦቹ በአሶሳ ከተማ ኢንቨስትመንትን ሽፋን በማድረግ ጥፋት ለመፈጸም ከህወሃት ድብቅ ትልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው።

ከዚህ ቀደም በክልሉ መተከል ዞን የተፈጸመውን ጥቃት ያስታወሱት ኮሚሽነሩ፤ ግለሰቦቹ ይህንን ጥፋት ዳግም ማስቀጠል ዋነኛ ግባቸው እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ግለሰቦቹ “ከመስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ መንግስት የለም” በሚል ከሃገር ውስጥ እና ከውጪ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ከሚሠራው የጥፋት ሃይል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የፖሊስ ኮሚሽነሩ አመልክተዋል፡፡

ግለሰቦቹ የአካባቢውን ወጣቶች በድብቅ በመመልመል ተጨማሪ ግጭት ለማስከተል ገንዘብ እና ሌሎችንም ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ እንደነበር የሚያመላክት መረጃ ፖሊስ ማግኘቱን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም የክሉልን መንግስት ውጥረት ውስጥ በማስገባት ስልጣን ማስለቀቅና በአካባቢው ትርምስ እንዲፈጠር ማድረግ የግለሰቦቹ ፍላጎት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

“ይህ ሁኔታ እንዲፈጸም የክልሉ ጸጥታ ሃይል በፍጹም አይፈቅድም” ያሉት ኮሚሽነሩ መንግስት መኖሩን ብቻ ሳይሆን በአጥፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድም ጭምር የህዝብ ደህንነት በማስጠበቅ ሠላም ማረጋገጡን እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ትብብሩን እንዲያጠናክርም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ:- ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top