Connect with us

የሐዘን_መግለጫ

የሐዘን_መግለጫ
Photo: Social media

ዜና

የሐዘን_መግለጫ

የሐዘን_መግለጫ

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በማውገዝ የተሰማቸውን ሃዘንም ገልፀዋል፡፡

በጥቃት አድራሽ አካላት ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጥቃት እጅጉን የሚያሳዝንና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ነው ብለዋል፡፡

ጥቃቱ ፍፁም ሰላማዊ በሆኑ ንፁሃን ዜጎች ላይ የተቃጣ መሆኑ አጥፊ ቡድኑ የሚከተለው መንገድ ኋላ ቀርና ጭካኔ የተሞላበት መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ሰላማዊ ህዝብን በመጨፍጨፍና በማስጨፍጨፍ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ሰው የመሆን ስብዕና የጎደላቸው ቡድኖች አፀያፊ ድርጊት ለክፍለ ዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያውያን አንድነትና ወንድማማችነት ሊቀይረው እንደማይችል ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የጥፋት ሃይሎችን በጋራ በመዋጋት አገሪቱ የዜጎች ደህንነት የተረጋገጠባት እንድትሆን ሁሉም በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡

ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡(ጋምቤላ ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top