Connect with us

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋሉ፡- ቱሪዝም ኢትዮጵያ

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋሉ፡- ቱሪዝም ኢትዮጵያ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ባህልና ታሪክ

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋሉ፡- ቱሪዝም ኢትዮጵያ

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋሉ፡- ቱሪዝም ኢትዮጵያ

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረጉ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በአገሪቱ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለቱሪስት ዝግ ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል።

በዚህም በአገሪቱ ዙሪያ የሚገኘው የቱሪስት መስህቦች ደረጃ በደረጃ ወደ ስራ እየተመለሱ ይገኛሉ።

ቱሪዝም ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ላልይበላ ከተማ በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት በጎብኚዎች ደህንነት አጠባበቅ፣ ለቱሪስት መረጃ አሰጣጥ እና በአገር አቀፍ የቱሪዝም መለያ /ብራንድ/ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በላልይበላ እና በደባርቅ አከባቢ ለተወጣጡ ከ600 በላይ ለሆኑ አስጎብኚዎች፣ የሆቴል ባለቤት ተወካዮች፣ ድጋፍ ሰጪዎች እና የደህንነት ጠባቂ ባለሙያዎች ነው ስልጠናው የተሰጠው።

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ እንዳሉት  የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትም ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረግ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ውቅር  አብያተ ክርስቲያናቱ  መከፈታቸውን አስመልክቶ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የሚገኙበት መርሃ ግብር ይካሄዳል ብለዋል። (EBC)

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top