Connect with us

የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሱዳን ገቡ

የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሱዳን ገቡ
Photo: Social Media

ዜና

የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሱዳን ገቡ

የሱዳን መንግሥት የሚያስተዳድረው የዜና ማሰራጫ እንደዘገበው የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በሁለቱ አገሮች የጸጥታ እና ወታደራዊ ትብብር ላይ ይመክራል። የደቡብ ሱዳን የመከላከያ እና ጡረተኛ ወታደሮች ጉዳይ ምኒስትር አንጌሊና ጄኒ ቴኒ ትናንት ወደ ኻርቱም አቅንተው ከሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል ቡርኻን ተገናኝተው ነበር።

በግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል መሐመድ ፋሪድ የሚመራ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑካን ቡድን ሱዳን ገባ። ልዑካን ቡድኑ ኻርቱም ሲደርስ የሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሉቴናንት ጄኔራል መሐመድ ኦስማን አል-ሁሴይን እንደተቀበሉት የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የሱዳን መንግሥት የሚያስተዳድረው የዜና ማሰራጫ እንደዘገበው የግብጽ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በሁለቱ አገሮች የጸጥታ እና ወታደራዊ ትብብር ላይ ይመክራል።

ሱዳን እና ግብጽ የሚሳተፉበት የታላቁ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ሲጀመር የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን ወደ ካይሮ አቅንተው ነበር። በጉዟቸው ከግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል ሲሲ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

የደቡብ ሱዳን የመከላከያ እና ጡረተኛ ወታደሮች ጉዳይ ምኒስትር አንጌሊና ጄኒ ቴኒ ትናንት ወደ ኻርቱም አቅንተው ነበር። ምኒስትሯ በኻርቱም ቆይታቸው ከሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል ቡርኻን ተገናኝተው እንደተወያዩ የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ከአንጌሊና ጄኒ ቴኒ በተጨማሪ ሱና እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የአገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትሮች ፣ የአገሪቱ የፖሊስ አዛዥ፣ የጸጥታ እና ደሕንነት መሥሪያ ቤት መሪዎችም ወደ ሱዳን ተጉዘዋል።
DW

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top