Connect with us

“የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ነው

"የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ" በሚል የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ነው
Ethiopian News Agency

ዜና

“የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ነው

“የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ነው

የጋራ ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠርና የውይይትን ባህል ለማዳበር ያለመ የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ  ነው፡፡ጉባኤው ከኦሮሞና ከአማራ መድረክ ወደ አገራዊ መድረክ በመሸጋገሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የህዝብ ለህዝብ መድረኩ አወያይ ዶክተር ዲማ ነጋዎ የዲሞክራሲን ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ በሚል የህዝብ ለህዝብ ጉባኤ በአዳማ  ዛሬ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ሲካሄድ እንደገለጹት፤ የኦሮሞና የአማራ የፖለቲካ ድርጅቶች ውይይት የጀመሩት የዛሬ ዓመት አካባቢ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ከፍተኛ ተቋማት በሚገኙ ተማሪዎች የተነሳውን ውዝግብ ተከትሎ ችግሩን ለማርገብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀረበ አነስሽነት ነው፡፡

ይህ የውይይት መድረክ ብዙ ስምምነቶች የተደረሱበት ሲሆን በሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ምሁራንና ሽማግሌዎች ተወስኖ የቆየው ወደ አገራዊ መድረክ እንዲሸጋጋር ተደርጓል፡፡

ይህም በአገራችንን ያለውን የፖለቲካ የውይይት ባህል ለማዳበርና ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር ይረዳል ብለዋል፡፡

ሌላው የመድረኩ አወያይ ዶክተር ገበያው ጥሩነህ በበኩላቸው የአሮሞና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጀመሩት ውይይት ፍሬ አፍርቶ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ደርሰዋል ብለዋል፡፡የዚህ ፍሬ አንዱ ውጤትም በሁለቱ ተወስኖ የነበረው ውይይት ወደ አገራዊ ውይይት ማደጉን በአብነት ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመካሄድ ላይ ያለው አገራዊ የፖለቲካ ሽግግርና የለውጥ ሂደት መልካም አጋጣሚዎች በመጠቀም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት  በአገራዊ የፖለቲካ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች የምክክር መድረኮች በመካሄድ ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በአማራና በኦሮሞ ማህበረሰቦች የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሁለቱ ብሄሮች ምሁራንና ተጋባዥ እንግዶች፣ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ የሁለቱ ህዝቦች ሁሉን አቀፍ ግንኙነቶች የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከታህሳስ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተደጋጋሚ ውይይቶችና ጉባኤዎችን አካሄደዋል፡፡

በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች በክልላዊና አገራዊ ነባራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ምክክር ሲያደርጉ ቆይተው በበርካታ ፖለቲካዊ አቋሞች ላይ የጋራ መግባባት በመድረስ መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም ታሪካዊ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

በመድረኩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምሁራን ታዋቂ ሰዎች፣የሲቪል ማህበራት፣ወጣቶች፣ሴቶችና የብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች እንደታሰተፉ ታውቋል፡፡(ኢኘድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top