Connect with us

ጀግኒት! እህታችን አክሱማዊት አብርሀ ምስጋናና አድናቆት ይገባታል!!

ጀግኒት! እህታችን አክሱማዊት አብርሀ ምስጋናና አድናቆት ይገባታል!!
Photo: Social Media

ማህበራዊ

ጀግኒት! እህታችን አክሱማዊት አብርሀ ምስጋናና አድናቆት ይገባታል!!

#ጀግኒት!

የዛሬ ሁለት አመት አካባቢ ቤተሰቦቿን ልትጠይቅ ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ተጓዘች። በቆይታዋም አንድ ቀን በአካባቢው የሚገኘውን ትምህርት ቤትን ልትጎበኝ ከቤት ወጣች።

ከጭቃና ከእንጨት የተሰራው ይሄው ት/ቤት አገልግሎቱን ጨርሶ ፈርሶ ሊወድቅ እንኳን ለተማሪዎቹ ለአስተማሪዎቹም ከባድ ስጋት ሆኖ ነበር። .… ምንም እንኳ እሷ ለዩኒቨርስቲ መምህርነት የበቃች ብትሆንም እነዚህ ህጻናት በዚህ አይነት ሁኔታ እየተማሩ አይታ ችላ ልትል እዕምሮዋ ፈጽሞ አልፈቀደላትም። .…ቤት ገብታ አሰላሰለች። ከራሷ ጋር ብዙ ተማከረች። “ምን ማድረግ እችላለሁ?” አሰበች፤ ከዝያም ወሰነች።

ቤተሰቦቿን፣ ወዳጅ ዘመዶቿን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ማስተባበር ጀመረች።….… ግማሽ ህልሟ ተሳካላትና ልክ በአመቱ አራት ዘመናዊ ክፍሎች ያሉት አንድ ብሎክ ጨርሳ አስረከበች።

ይህንኑ ጥረቷን አጠናክራ በመቀጠል ዘንድሮ ደግሞ ሌላውን ባለ አራት ክፍል አንድ ብሎክ በማገባደድ “ልውደቅ ልቅር” እያለ ለህጻናቱ፣ ለወላጆቻቸውና ለት/ቤቱ ማህበረሰብ ስጋት የነበረውን ቀይ አምባ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ሙሉ በሙሉ በአዲስ ህንጻ ገንብታ አጠናቀቀች።

አሁን 650 ተማሪዎች ያለስጋት በመማር ወደ ነገ ህልማቸው ይንደረደራሉ። “በስተመጨረሻ ምን ተሰማሽ?” ስላት “እረፍት” አለችኝ ‘የህሊና እረፍት።’

– ወጣት የነብር ጣት ይሏል እንዲህ ነው! ህልሙን ለማሳካት ከተነሳ ምንም አይነት ምድራዊ ሀይል አይገድበውም! ይህን ታላቅ ገድል የፈጸመች፣ ለብዙዎቻችን ምሳሌ የምትሆን እህታችን አክሱማዊት አብርሀ ምስጋናና አድናቆት ይገባታል!!

(#የትነበርክታደለ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top