Connect with us

“የዶናልድ ትራምፕን ንግግር ተከትሎ ለሚመጣ ነገር  አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን” – የኢፌዴሪ አየር ሃይል

"የዶናልድ ትራምፕን ንግግር ተከትሎ ለሚመጣ ነገር  አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን" - የኢፌዴሪ አየር ሃይል
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

“የዶናልድ ትራምፕን ንግግር ተከትሎ ለሚመጣ ነገር  አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን” – የኢፌዴሪ አየር ሃይል

“የዶናልድ ትራምፕን ንግግር ተከትሎ ለሚመጣ ነገር  አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን” – የኢፌዴሪ አየር ሃይል

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግር በአገር ሉአላዊነት ላይ የተቃጣ በመሆኑ ይህንን ተከትሎ ለሚመጣ ነገር ሁሉ አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዝግጁ መሆኑን አስታወቀⵆ

የኢፌዴሪ አየር ሃይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር ሀያል አገርን እመራለሁ ከሚል ፕሬዝደንት የሚጠበቅ አይደለም።

የአንድን አገር ሉአላዊነት በንግግርም ቢሆን መጣስ ከባድ ጥፋት በመሆኑ ይህንን ተከትሎ ሊመጣ የሚችል ማንኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመመከት አየር ሃይሉ ሙሉ ዝግጁነት አለውⵆ

እንደ ሜጀር ጀነራል ይልማ ገለጻ፤ ለፕሬዝዳንቱ ንግግር የአገር መሪዎችና ዲፕሎማቶች በዲፕሎማሲው መድረክ መልስ እንደሚሰጡ ሁሉ፤ አየር ሃይሉ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ለጎሰሙት የጦርነት ነጋሪት አስፈላጊውን መልስ ይሰጣልⵆ

“ከአባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ ጭቅጭቅ እያነሱ ያሉ አካላት ከ2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው በእግረኛ ጦር ይዋጋሉ ብለን አናስብም፤ በመሆኑም ወደ ግጭት ከተገባም ግጭቱ በቀጥታ ከአየር ሃይል ጋር እንደሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ደረጃ እነሱ ምንድን ነው ያላቸው? የመሳሪያ ቴክኖሎጂያቸው፤ የሰው ሃይል ብቃት የስልጠና ደረጃቸው ምን ይመስላል? የሚለውን ለይተን እናውቃለን። ከዚህም ባሻገር 24 ሰዓት ዓይናችን የህዳሴው ግድብ ላይ ነው” ብለዋል አዛዡ።

የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ብቃት እኛ ከምናውቀው በላይ እነሱ ጠንቅቀው ያውቁታል፤ ስለወደዱን ወይም አቋማችንን ስለተቀበሉ ሳይሆን ሁኔታዎች ወዴት ሊሄዱ እንደሚችሉ ጠንቅቀው ስለሚያውቁም ጭምር የሚፈጠር ጉዳይ አይኖርም ያሉት ሜጀር ጀነራል ይልማ፤ አየር ሃይሉም ለ24 ሰዓታት ለሰባት ቀናት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌለው ሀብት ላይ ቆጥቦ እየገነባው ያለው ፕሮጀክቱ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ቢሆንም፤ አየር ሃይሉ ግን በጠቅላላው የአገሪቱን መሰረተ ልማቶች፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እንዲሁም ወታደራዊ ማዕከሎችን በንቃት እንደሚጠብቅም አረጋግጠዋልⵆ (EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top