Connect with us

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መልዕክት

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መልዕክት
Ethiopian News Agency

ዜና

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መልዕክት

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መልዕክት

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ  ነገ ሀሙስ ጥቅምት 19/2013 ዓ.ም የሚከበረውን 1 ሺህ 495ኛው የነብዩ ሙሀመድ መውሊድ በዓልን በማስመልከት ካስተላለፉት መልዕክት:-

‘~ ‘አንዱ አንዱን መግደል የሰው ልጆች ባህሪ ባለመሆኑ ሊቆም ይገባል”  

~  “ነብዩ ሙሀመድ በምድር ቆይታቸው በጎ ነገሮችን ሰርተው አልፈዋል፤ በመወለዳቸው ምክንያት የሰው ልጅን መከራን አስቀርተዋል”

‘~ ‘ነብዩ ሙሀመድ የሰውን ልጅ ከጥፋት መልሰውታል በዚህም ይደርስበት የነበረው ርሃብና ድርቅም ተነስቶለታል” 

~ ”ማንም ሰው በህይወት እስካለ ድረስ የነብያችንን አደራ፣ አመራርና መልካም ጠባይ ሊከተል ይገባል”

~ “ኢትዮጵያዊያን መተዛዘን፣ አብሮ መብላት፣ መረዳዳት እንጂ መገዳደል፣ ደም መቃባት ባህላችን አይደለም….ወደ አውሬነት ልንመለስ አይገባም” 

~ ’ሁላችንም ሰላማችንን መጠበቅ በመከባበርና መተዛዘን አንድነትን በማጠናከር የድርሻችንን እንወጣ’’

~ ሰው ከሀጥያት እስካልተቆጠበ ድረስ ወደፊት ከአንበጣ በተጨማሪ ሌላ መከራ ሊመጣ እንደሚችል፤ ‘’የእምነቱን አስተምህሮ በመከተል ከሙስና፣ ከሌብነትና በደል ራስን ማራቅ ያስፈልጋል’’ 

~ በአባይ ውሃ ላይ ለመጠቀም የተጀመረውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰጡት አስተያየት የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው ነው፣

(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top