Connect with us

የኅዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ መካከል የሚደረገው ድርድር ነገ ይጀመራል

በታላቁ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ መካከል የሚደረገው ድርድር ነገ ይጀመራል
Photo: Social media

ዜና

የኅዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ መካከል የሚደረገው ድርድር ነገ ይጀመራል

በታላቁ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ መካከል የሚደረገው ድርድር ነገ ይጀመራል

ፕሬዝዳንቱ ለሰባት ሳምንታት ተቋርጦ የቆየው ድርድር ነገ መቀጠሉን ይፋ ያደረጉት ዛሬ ባወጡት መግለጫ ነው።

የአፍሪካ ኅብረትን በሊቀ-መንበርነት በመምራት ላይ የሚገኙት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እንዳሉት “በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የሚደረገው ድርድር መቀጠል የሶስቱ አገሮች መሪዎች በታላቁ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ከሰላማዊ እና አግባቢ መፍትሔ ለመድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ይጠቁማል።”

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው አርብ ግብጽ ግድቡን “ታፈነዳለች” ሲሉ የሰጡት አስተያየት ኢትዮጵያን አስቆጥቶ ነበር። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ገዱ አንዳርጋቸው ትራምፕ የሰጡትን አስተያየት “በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ጦርነት ቀስቃሽ” ሲሉ ከሰዋል።

“ጊዜው የተግባር እንጂ ውጥረት የሚባባስበት አይደለም” ያሉት የአውሮፓ ኅብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል የአፍሪካ ኅብረት በጀመረው ሶስቱን አገሮች የማደራደር ጥረት እንዲገፋበት መክረዋል። ጆሴፕ ቦሬል እንዳሉት”የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበር የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ሁሉንም ወገኖች መፍትሔ እንዲያበጁ ለማደራደር የጀመረችው ጥረት የአውሮፓ ኅብረት ሙሉ ድጋፍ አለው።”

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዛሬ ባወጡት መግለጫ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በሰጡት አወዛጋቢ አስተያየት ላይ ምንም ያሉት ነገር የለም። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ ሶስቱ አገሮች ድርድሩን ለመቀጠል መስማማታቸው በፓን አፍሪካዊ መርኅ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ለመፈለግ ያላቸውን በራስ መተማመን ማረጋገጫ ሲሉ አወድሰዋል። ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ “ቴክኒካዊ እና ሕጋዊ ጉዳዮችን ጨምሮ በቀሩ ጉዳዮች ላይ በድርድሩ ከሥምምነት እንደሚደርሱ” ተስፋቸውን ገልጸዋል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top