Connect with us

ሲኖትራክ የ10 ዓመት ታዳጊ ሕይወት ነጠቀ

ሲኖትራክ የ10 ዓመት ታዳጊ ሕይወት ነጠቀ
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

ዜና

ሲኖትራክ የ10 ዓመት ታዳጊ ሕይወት ነጠቀ

ሲኖትራክ የ10 ዓመት ታዳጊ ሕይወት ነጠቀ

በቦሌ ክ/ከተማ በመኖሪያ ቤት እና  በንግድ ሱቅ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የ10 ዓመት ህፃን ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ ።                  

አደጋው የተከሰተው ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ገደማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 በልዩ ስሙ ሪፌንቲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መርማሪ ምክትል ሳጅን ታምራት መስፍን እንዳስረዱት በሰሌዳ ቁጥር  ኮድ  3 -61312 ኢ.ት  ሲኖትራክ ተሽከርካሪ  የመንገድ ጠርዝ ስቶ አንድ ላይ ተያይዘው የሚገኙ የመኖሪያ ቤት እና የንግድ ሱቅ ጥሶ በመግባት ባደረሰው አደጋ  ወደ ሱቁ ተልኮ የመጣ አንድ የ10 ዓመት ህፃን ልጅ ህይወት ሲያልፍ በሁለት ግለሰቦች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም ከፍተኛ የንብረት ውድመት ተከስቷል፡፡

በአደጋው የንብረት መውደም ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ሰቦቃ ለታ እና ወ/ሮ ሰሚራ ሰይድ  አደጋውን በተመለከተ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ባልታሰበ ሁኔታ ድንገት ባጋጠመ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና አካል ላይ የደረሰው ጉዳት አስከፊ መሆኑን ገልፀው  ሌሎች ህፃናትን ይዘን ባንሸሽ ጉዳቱ እጅግ የከፋ ሊሆን ይችል ነበር ብለዋል፡፡ 

በሰው ህይወትና በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ አሽከርካሪዎች በሀላፊነት ስሜት ሊያሽከረክሩ እንደሚገባ ምክትል ሳጅን ታምራት መስፍን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

(አ/አ ፖሊስ ኮሚሽን)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top