Connect with us

አወዛጋቢ ውሳኔ የያዘው ደብዳቤ ተሻረ

አወዛጋቢ ውሳኔ የያዘው ደብዳቤ ተሻረ
Photo: ዱቤ ጅሎ ምክትል ኮሚሽነር

ስፖርት

አወዛጋቢ ውሳኔ የያዘው ደብዳቤ ተሻረ

አወዛጋቢ ውሳኔ የያዘው ደብዳቤ ተሻረ

የአትሌቲክስ እና እግርኳስ ፌዴሬሽኖች እንደማይቀበሉት የገለፁት የትግራይ ስፖርት ተቋማትን ከፌደራል ስፖርት ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም የሚል ብዥታ ፈጥሮ የነበረው ውሳኔ ተሻረ፡፡

በትላንቱ ፅሁፌ ከፌደራል ስፖርት ኮሚሽን 9/2/2013 የወጣው የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ ተፈጻሚ አድርጉ በሚል ለኢትዮጵያ ኦሎምፒክ እንዲሁም ፓራሊምፒክ ኮሚቴን ጨምሮ ለ20 ፌዴሬሽኖች እና 8 አሶሴሽኖች የተላከው ደብዳቤ የህግ ትርጉም ክፍተት አለው ስል ነበር፡፡

ይኸው ዛሬ ኮሚሽኑ ባወጣው ደብዳቤ ውሳኔውን ሽሮታል፡፡  

ቀደም ሲል የወጣውና የፌዴሬሽን ምክርቤት ባደረገው ስብሰባ የትግራይ ክልል በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ በአባሪ የያዘ ደብዳቤ መላኩን ያስታወሰው ኮሚሽኑ፣ የተጻፈውም ደብዳቤ የመረጃ ክፍተት ያለው በመሆኑ የተሻረ መሆኑን እወቁት ብሎአል፡፡

የትርጉም ክፍተት ነበረው አሊያም ተጨማሪ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባ ነበር በሚል የተሻረው ደብዳቤ  የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ከፓለቲካ እንቅስቃሴ ውጪ በሆኑትና በአደረጃጀትም ህዝባዊ መዋቅር ባላቸው ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን በዚህ ደረጃ ውዝግብ ከፈጠረ በሌሎች ውስብስብ የአፈፃፀም መመሪያ በሚጠይቁ ጉዳዮችማ ሊኖር የሚችለው ብዥታ ይታየኛል፡፡(ምንጭ:- ጋዜጠኛ ታደለ አሰፋ)

ፎቶ :- ዱቤ ጅሎ ምክትል ኮሚሽነር

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top