Connect with us

በአዲስአበባ በሶስት ወራት 10 ቢልየን ብር ተሰበሰበ

በአዲስአበባ በሶት ወራት 10 ቢልየን ብር ተሰበሰበ
Ethiopian News Agency

ኢኮኖሚ

በአዲስአበባ በሶስት ወራት 10 ቢልየን ብር ተሰበሰበ

በአዲስአበባ በሶስት ወራት 10 ቢልየን ብር ተሰበሰበ

በአዲስ አበባ ከተማ በመጀመሪያው ሩብ በጀት ዓመት 9 ነጥብ 99 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በ8ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው የአስፈጻሚ አካላትን የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው፡፡

የሴክተሮች የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ምክትል ከንቲባዋ ለምክር ቤቱ አባላት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በሪፖርታቸው እንደገለጹት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የ10 ነጥብ 87 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 9 ነጥብ 99 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለ280 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ በሩብ ዓመቱ ለ43 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩንም ገልጸዋል፡፡

የንግድ ስርዓቱን ከህገ ወጥነት ለመከላከል በተሰራው ስራም በ3 ሺህ 356 የንግድ ድርጅቶች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል ነው ያሉት፡፡

በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችም በጥሩ አፈጻጸም ላይ ናቸው። (ኢዜአ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top